ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
በዕውቀቱ ሥዩም

“መግባት እና መውጣት” እና ሌሎች መጽሐፍት ደራሲ

በዕውቀቱ ሥዩም

[የትዉልድ ቀን] 0000-00-00
[አጭር መግለጫ]

በእውቀቱ ስዩም በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ዝነኛ ገጣሚያንና ደራሲያን አንዱ ነው። በተለይም ኮሜዲ አዘል በሆኑ መጣጥፎቹ ይታወቃል። በአዲስ ላይቭ ኢንተርኔት ሬዲዮ በእሱ በራሱ ወይም በመስታዎት አራጋዉ ይቀርቡ በነበሩ ትረካዎቹም ታዋቂነትን አትርፏል። በሲዲ በተለቀቁ የኮሜዲ ሥራዎች ላይም እንደ ደረጀ ኃይሌ፣ ፈቃዱ ከበደ እና ሌሎች ታዋቂ ኮሜዲያን ጋር ተሳትፎ አለው።
“ኗሪ አልባ ጎጆዎች”፣ “በራሪ ቅጠሎች” እና “የእሳት ዳር ሀሳቦች” የተባሉ የግጥም መጻሕፍት ሲኖሩት፣ እነዚህን በአንድ ላይ አሰባስቦ “ስብስብ ግጥሞች” ብሎ አሳትሟል። ከዚህ በተጨማሪ “መግባትና መውጣት”፣ “እንቅልፍና እድሜ” እንዲሁም በ2008 ዓ.ም. ባወጣው “ከአሜን ባሻገር” በተሰኙ ሥራዎቹ ይታወቃል። በማስከተል “የማለዳ ድባብ” እና “አዳምኤል” የተባሉ የግጥም ስብስቦቹን ለኅትመት አበቃ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በመጽሔት፣ በጋዜጣ እና በማኅበራዊ መገናኛዎች እጅግ በጣም ብዙ አጫጭር ጽሑፎቹን እያቀረበ ይገኛል፡፡

[ከመጻሕፍቱ መካከል]
* ከአሜን ባሻገር
* መግባት እና መውጣት
* እንቅልፍ እና ዕድሜ
* የማለዳ ድባብ
* አዳምኤል

[መገኛዎቹ] ፌስቡክ፡ - https://facebook.com/search/top/?q=bewketu%20seyoum
[ምንጮቻችን] ከልዩ ልዩ ቃለ ምልልስ


ስለሌሎች ደራስያን እዚህ ይወቁ

መጻሕፍት ከየምድባቸዉ ለመምረጥ እዚህ ይግቡ መጻሕፍት ከጠቅላላ ዝርዝር ለመምረጥ እዚህ ይግቡ
በዕውቀቱ ሥዩም
መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts