ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ቃለ ምልልስ

ከባለ ተሞክሮ አንጋፋዎችና ወጣቶች ጋር


ከጀርባ መሆን መልካም ነው።

ሄኖክ አየለ(አዘጋጅ)
Read in PDF 2021-09-02 በታደለ አያሌው
ሄኖክ አየለ(አዘጋጅ)

የሓ፡- ያዘጋጀሃቸው ፊልሞችን እኔ ስቆጥር ፲፩ ደረሱ። እስኪ ፊልሞችህን አስቆጥረኝ።

ሄኖክ:- ቁጠር። የመጀመሪያው ‹መስዋዕት›፣ ኹለተኛው ‹የወንዶች ጉዳይ፩›፣ ከዚያ ‹አልቦ›፣ ከዚያ ‹ፔንዱለም›፣ ከዚያ ‹ስብራት›፣ ከዚያ ‹ልክ ነኝ!›፣ ከዚያ ‹ይግባኝ›፣ ከዚያ በኋላ ‹ቀሚስ የለበስኩ 'ለት›፣ ቀጥሎ ደግሞ ‹አዲናስ› እና አሁንም ሌሎች ስራዎች ላይ ነኝ። ገመና፩ የቴሌቪዥን ድራማ ላይም በዝግጅት ነበርኩበት።

የሓ፡- እውነትም ልጆችህ ናቸው። አልፎ አልፎ ከፊልም ሰሪዎች የምታዘበው ‹‹ፊልሞቼ ልጆቼ ናቸው›› ካሉ በኋላ ዝርዝራቸውን እረሳሁ ሲሉ ነበር። እንዲህ በስስት ከነ ልደት ተራቸው መንገርህን አድንቂያለሁ። ያውም በድንገት፣ ባንድ ትንፋሽ!

ሄኖክ:- በል እርምህን አውጣ፣ ፊልሞቼን መቼም አልረሳልህ። እንኳን ርዕሳቸው ይቅርና የቀረጻ ዉጣ ውረዳቸው፣ የተዋንያኑን ነገር፣ የቦታ ቦታው ነገር፣ የአጋዦች እገዛ፣ የእንቅፋቶች ከፍታ ሁሉ አልረሳቸውም እኔ። ጊዜ ኖሮህ ባጫወትኩህ።

የሓ፡- ለምን ዳይሬክተር ብቻ ሆንክ ግን፤ ያውም የፊልም ብቻ?

ሄኖክ:- ሁሉንም ስለሚያካትት ነዋ። ዳይሬክተር ስለሆንኩ እኮ ተዋንያንንም፣ ደራስያንንም፣ ‹ፕሮዲዩሰሮችንም›፣ ሌሎችንም ቀድሞ የመምራት እድል አለህ። ስሜቴን፣ ሃሳቤን፣ ህልሜን አጋራበታለሁ። እና፤ ዳይሬክተር የሆንኩት አንድም ስለምወደው አንድም ስለምችለው ነው። ‹ለምን የፊልም ብቻ› ላልከው ግን እኔም እያሰብኩበት ነው። የተማርኩት እንዲያውም ቴአትር ስለሆነ፣ ወደ ፊት ቴአትርም አንድ መተንፈሻዬ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ።

የሓ፡- ደግም እኮ የፊልም ዳይሬክተር በኛ አገር አይደግምም ይባል ነበር። አንተ ከመድገምም እስከ አስራ አንድ ፊልሞች ደጋገምክሳ። ምኑ ቢረዳህ ነው ያን ያህል?

ሄኖክ:- ሌላም ስራ የለኝ እኔ። ሲደመር ተጨማሪ ያንብቡ


1 ከ 4

ከዚህ ቀደም አብረዉን ከተጨዋወቱ እንግዶች መካከል
ፈቃዱ ተ/ማርያም ቴአትር ልክፍት ነዉ፤ አንዳንዴ እንዲያዉም ጅል ያደርጋል፡፡
ፈቃዱ ተ/ማርያም Read in PDF

የሓ፡- በዋናነት ተዋናይ ብቻ ነህ ጋሽ ፍቄ። ግን የልብን ስሜት አውጥቶ ለመንገር ተዋናይነት ብቻ በቂ ነው?

ፈቃዱ፡- ሲቻል ነዋ ታዲያ። ጽሑፍ ወይ ሌላ ሙያ ላይ የለሁበትም ያን ያህል። ብችልና ተጨማሪ ያንብቡ

ግሩም ኤርሚያስ የጥበብ ሰው ጥግ የለውም፣ ከማኅበረሰብ ወዲያ፡፡
ግሩም ኤርሚያስ Read in PDF

የሓ፡- ብዙ ወጣቶች ፊልም መተወን እንደሚፈልጉ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ እነሱንና አንተን እንዲህ ወደ ትወና ያማለላችሁ ምኑ ደስ ቢል ነው?

ግሩም፡- ያልተኖረ ህይወት መኖር ስለሚያስችል ይመስለኛል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት እኔ የትም ቦታ ተማሪ ነኝ፡፡
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት Read in PDF

የሓ፡- የስራህ ብዛት ይታወቃል መቼም፡፡ የሃይማኖት መምህርነቱ አለ፣ ልጅ ታሳድጋለህ፣ ሰዎችን ታማክራለህ፣ መጽፎችን ትጽፋለህ፣ ጥናቶችን ታጠናለህ፣ የ‹አግዮስ ህትመት› ስራ አስኪያጅ ተጨማሪ ያንብቡ

መልእክተ የሓ

በዚህኛዉ ዐምድ እንዲጋበዙላችሁ የምትፈልጓቸዉን ሰዎች እንድትጠቁሙን ወይም ደግሞ የራስዎትን የህይወት ተሞክሮ ለማካፈል ፈቃደኛ ከሆኑ በዚህ በኩል ቢያገኙን ደስታዉን አንችለዉም፡፡

መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts