ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ቃለ ምልልስ

ከባለ ተሞክሮ አንጋፋዎችና ወጣቶች ጋር


እኔ የትም ቦታ ተማሪ ነኝ፡፡

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
Read in PDF 2015-07-14 በየሓ ቤተ ጥበብ
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

የሓ፡- የስራህ ብዛት ይታወቃል መቼም፡፡ የሃይማኖት መምህርነቱ አለ፣ ልጅ ታሳድጋለህ፣ ሰዎችን ታማክራለህ፣ መጽፎችን ትጽፋለህ፣ ጥናቶችን ታጠናለህ፣ የ‹አግዮስ ህትመት› ስራ አስኪያጅ ነህ፣ ካገር አገር ከክልል ክልል ትዞራለህ … ጊዜው ላንተ ይበዛልሃል ልበል?

ዲ/ን:- ለእያንዳንዱ አዋዋሌ መርሐ -ግብር ስላለኝ ይመስለኛል፡፡ ነውም ደግሞ፡፡ ሰዎችን ለማማከርም ቀን መድቢያለሁ፡፡ ለሌላውም እንዲሁ ሰዐት ቆርጨለታለሁ፡፡ እንጂ እንዳልከው አልፎ አልፎ ሰበር የሚገቡ ‹ፕሮግራሞች› አሉ፡፡ ከመንግስት የሚመጡ፣ ከተለያዩ ድርጅቶች የሚመጡ፣ ከዐለም አቀፍ ድርጅቶች የሚመጡ፣ ከሃይማኖት ተቋማት የሚመጡ በጣም ብዙ ጉዳዮች አሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ እንደጠቃሚነታቸውና እንዳስቸኳይነታቸው ከመደበኛ ተግባሮቼ ጋር አስተያያለሁ፡፡ እንዲህ ሲሆን ደግሞ ሰዐቱ ከበቂም በላይ ነው፡፡

የሓ፡- የበጎ ሰው ሽልማት ዘንድሮ አልዘገየም?

ዲ/ን:- ዘግይቷል፡፡ የዘገየው ግን በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ አንደኛው የምርጫው ነገር ሲሆን ኹለተኛው ደግሞ በመሀል ያጋጠመን በሊቢያ የሆነብን ሃዘን ነው፡፡ በሁለቱ ኩነቶች መካከል ሽልማቱ ዘገየ፡፡ ነገር ግን አሁን እየመጣ ነው፡፡ በሚቀጥለው ሳምንት እጩዎቹ ታውቀው ይገለጡና ዋናው ሽልማት ነሐሴ ወር ማብቂያ ላይ ይካሄዳል፡፡

የሓ፡- ሦስት ድኅረ ገጾች አሉህ፡፡ ‹የዳንኤል ክብረት እይታዎች›፣ ‹አግዮስ› እና ‹የበጎ ሰው ሽልማት› የሚሉ፡፡ በተለይ ኹለቱን የመጎብኘትህ ነገር ግን ቀዝቅዟል፡፡ አንዱስ አይበቃህም ነበር?

ዲ/ን:- ሦስት የሆኑ ለሦስትነታቸው ነው፡፡ የተለያየ ነው ስራቸው፡፡ እንዳልከው ግን አግዮስ ብዙም አልተከታተልኩትም፡፡ ያ የሆነበት ምክንያትም በ‹ቴክኒክ› ክፍተት ነው፡፡ በቅርቡ ግን ሦስቱም እንደጠባያቸው ተጨማሪ ያንብቡ


4 ከ 4

ከዚህ ቀደም አብረዉን ከተጨዋወቱ እንግዶች መካከል
ፈቃዱ ተ/ማርያም ቴአትር ልክፍት ነዉ፤ አንዳንዴ እንዲያዉም ጅል ያደርጋል፡፡
ፈቃዱ ተ/ማርያም Read in PDF

የሓ፡- በዋናነት ተዋናይ ብቻ ነህ ጋሽ ፍቄ። ግን የልብን ስሜት አውጥቶ ለመንገር ተዋናይነት ብቻ በቂ ነው?

ፈቃዱ፡- ሲቻል ነዋ ታዲያ። ጽሑፍ ወይ ሌላ ሙያ ላይ የለሁበትም ያን ያህል። ብችልና ተጨማሪ ያንብቡ

ግሩም ኤርሚያስ የጥበብ ሰው ጥግ የለውም፣ ከማኅበረሰብ ወዲያ፡፡
ግሩም ኤርሚያስ Read in PDF

የሓ፡- ብዙ ወጣቶች ፊልም መተወን እንደሚፈልጉ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ እነሱንና አንተን እንዲህ ወደ ትወና ያማለላችሁ ምኑ ደስ ቢል ነው?

ግሩም፡- ያልተኖረ ህይወት መኖር ስለሚያስችል ይመስለኛል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት እኔ የትም ቦታ ተማሪ ነኝ፡፡
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት Read in PDF

የሓ፡- የስራህ ብዛት ይታወቃል መቼም፡፡ የሃይማኖት መምህርነቱ አለ፣ ልጅ ታሳድጋለህ፣ ሰዎችን ታማክራለህ፣ መጽፎችን ትጽፋለህ፣ ጥናቶችን ታጠናለህ፣ የ‹አግዮስ ህትመት› ስራ አስኪያጅ ተጨማሪ ያንብቡ

መልእክተ የሓ

በዚህኛዉ ዐምድ እንዲጋበዙላችሁ የምትፈልጓቸዉን ሰዎች እንድትጠቁሙን ወይም ደግሞ የራስዎትን የህይወት ተሞክሮ ለማካፈል ፈቃደኛ ከሆኑ በዚህ በኩል ቢያገኙን ደስታዉን አንችለዉም፡፡

መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts