ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
አዲሱ መጽሐፍ

በዚህ ሳምንት የወጡ አዳዲስ መጽሐፍት ይተዋወቁበታል

ገረገራ

[ርዕሥ] ገረገራ
[ደራሲ] ታደለ አያሌው
[አርታዒ] ኃይለ መለኮት መዋዕል
[ምድብ] ልብ ወለድ
[ዘዉግ] ስለላ፣ ሴራና ምስጢራዊ
[አሳታሚ] የሓ ቤተ ጥበብ
[የመጀ.ዕትም] 2014-07-10
[አሁን የደረሰበት] 1ኛ ዕትም
[ISBN (መለያ)] 978-99944-3-533-3
[የገጽ ብዛት] 244
[የሽፋን ዋጋ] 180
[መሸጫ ዋጋ] 150

[ቅንጭብ]

ብቻ አትቀደሚ! አንዴ አይቅደሙሽ እንጂ፣ ከተቀደምሽ አንቺን ለመድፈቅ የማይበረታ የለም። ሳር ቅጠሉ ይነሳብሻል። ምናምንቴዉ ሁሉ ጎሮሮሽ ላይ ይቆማል። እንኳንስ የኔ ነዉ የምትዪዉ ይቅርና፣ ራሳቸዉ ያንቺ ነዉ ያሉሽን እንኳን ይወስዱብሻል። ጭራሽ ባዶሽን ማስቀረታቸዉም አልበቃ ብሏቸዉ፣ ወሰደችብን ብለዉ ያዋክቡሻል። መልሰዉ ደግሞ ይዘባበቱብሻል። ይሸልሉብሻል። ግድየለም እነሱን ራሳቸዉን እንኳን አጥቻቸዉ የለ ብለሽ እንኳን እንዳትጽናኝ፣ የመጽናኛ ትንፋሽ የሚባል አያስቀሩልሽም። አንቺን በፍህም ያዉም በሹል ሚስማር ላይ አቁመዉሽ፣ ያሽካኩብሻል። ልንገርሽ? በፍጹም እንዳትቀደሚ። ወደ አንቺ የተዘረጋዉ እጅ ለፍቅርም ይሁን ለጸብ፣ እንዳመጣጡ አፈፍ አድርጊዉ እንጂ አትቀደሚ። ለምንም ነገር፣ ማንም አይቅደምሽ! የፈለገ ምን ብትሸሸዉ፣ ዉጊያዉ እንደሆነ አይቀርልሽም እንግዲህ! ይልቁንስ ምረጪ። መዋጋት ያለብሽ ራስሽን ለማዳን ነዉ ወይስ ራሱን የሚዋጋሽን ቤተሰብ ለማትረፍ? ወጣ ወረደ፣ እንዳትቀደሚ!

[በገበያ ላይ የት የት አለ?]

በክፍለ ሀገር (በብዙ ከተሞች)
•ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ሀዋሳ፣ ደ/ማርቆስ፣ አዳማ/ናዝሬት እና በሌሎችም ከተሞች
በአዲስ አበባ (በአብዛኛዉ አብያተ መጻሕፍት)
| ሜክሲኮ|
•ሀሁ (አዲሱ የደ/ወርቅ ህንጻ ሱቆች)
•ሔመን(አዲሱ የደ/ወርቅ ህንጻ ሱቆች)
•ኮሜርስ (ከቴሌባር ወደ ቡናና ሻይ መዞሪያዉ ዘንድ)
| ለገሀር|
•ጃፋር (ኖክ አጠገብ፣ ተወልደ ህንጻ ሥር)
•ሠዐዳ (ከጃፋር አጠገብ)
| ስቴዲየም|
•ሀሁ (የንግድ ባንክ ዋናው ቅርንጫፍ ጀርባ)
•እዉቀት በር (ወጋገን ባንክ አልፎ፣ መብራቱ ጋ ሳይደርስ)
| ብሔራዊ|
•ዓይናለም (አዋሽ ባንክ ጎን፣ በቴአትር ቤቱ ጀርባ)
•ዮናስ (ቴአትር ቤቱ በረንዳ ላይ፣ በራስ ሆቴል ሆቴል በኩል)
| ጥቁር አንበሳ|
•ሊት ማን (ትራኮን ታወር 1ኛ ፎቅ)
| አውቶብስ ተራ|
•አስቻለው መጽሐፍ ቤት
| ፒያሳ|
•ኤዞጵ (አቡነ ጵጥሮስ ከፍ ብሎ)
•ሙሉነሽ (ወደ ሀገር ፍቅር መውረጃው)
•ጌታቸው (ወደ ሀገር…)
| አራት ኪሎ|
•አበራ (ቅ/ማርያም ካፌ ገባ ብሎ)
•እነሆ (ማለዳ ካፌ አጠገብ)
•ዋልያ (ዳኑ ሆሰስፒታል ጎን፣ ኢክላስ ህንጻ)
•ጸጋዬ (ኢክላስ ህንጻ)
| አምስት ኪሎ|
•አበራ (ብ/ ሙዝየም ፊት ለፊት፣ ተስፋ ቡና ጎን)
•ብራና (ዋናዉ የማኅበረ ቅዱሳን ህንጻ ጎን)
| ካዛንቺስ|
•ጦቢያ (መላ ህንጻ)
| መገናኛ|
•ሽታዬ (ዘፍመሽ ፊት ለፊት፣ በንብ ባንክ ገባ ብሎ)
| ቦሌ|
•ሽታሁን (ከሰላም ሲቲ ሞል ጎን)

እዚህ ላይ ይግዙት

ሌሎች መጽሐፎች ይምረጡ

መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts