አዲሱ ቴአትር
በዚህ ሳምንት የወጡ አዳዲስ ቴአትሮች ይተዋወቁበታል
ሸምጋይ
[ርዕሥ] | ሸምጋይ |
[ደራሲ] | ታደለ አያሌዉ |
[አርታዒ] | ሳሙኤል ተሥፋዬ |
[አዘጋጅ] | ሳሙኤል ተሥፋዬ |
[ረዳት አዘጋጅ] | ስናፍቅሽ ተሥፋዬ |
|
|
[ዘዉግ] | ታሪክ ቀመስ (ትዉፊታዊ) |
[ፕሮዲዩሰር] | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር |
[የመክፈቻ ቀን] | ታኅሣሥ 27፣ 2015ዓ.ም |
[ድራማተርጅ] | ኢዮብ ገረመዉ |
[ተዋንያን] | ብርሃን ተሥፋዬ፣ እታፈራሁ መብራቱ እና ሌሎች (20+) |
|
|
[የደራሲዉ ቀዳሚ ሥራዎች] | ረበናት (2011፣ ልብ ዉለድ) ገረገራ (2014፣ ልብ ዉለድ) |
|
|
[ቅንጭብ] |
ገብረ ሐና፡- /ደስ ደስ አላቸው/ አዛኜን?
ተክሌ፡- አዛኜን! ሌላው እምቢ እንዳለ ቢቀር እንኳን፣ የነፍስ ጥበብ መሆኑን ነው ልቤ እሚለኝ። ፍቃድዎ ቢሆንማ ቢያስጠኑኝ ነበር ደስታዬ። ብቻ ግን ተከልክሏል ያው …
ገብረ ሐና፡- ካጠናኸውማ በስምህ ዝማሜ አቆምን በለኛ። ‹‹የተክሌ ዝማሜ›› መባሉ ነዋ። /ጥሩነሽን እቅፍ አድርገው ሳሟትና/ ጥሩዬ … ከደጅ ሳትርቂ ልጆች ፈላልጊና እየተጫወትሽ ሠው ወደዚህ ሲመጣ ካየሽ ሮጠሽ ንገሪን። እሺ?
ጥሩነሽ፡- ለኔም ካለማመዱኝ…
ገብረ ሐና፡- ኋላስ! እኔው አስቀጽልሻለሁ።
/በደስታ እየዘለለች ወጣች። ወደ ታችኛው መስኮት ቸኩለው ወሰዱትና።/
ተክሌ፡- ና እስኪ ወዲህ። አየኸው ያን ሸንበቆ? አየኸው? እየውማ። … እርቡቅ አለ ወደ ምድር። ቀና አለ ላንፋውን በሞገስ ዘርግቶ። ወደ ግራ ዘመመ በዝግታ። ወደ ቀኝ መለስ አለ እንደገና። አየኸው?
/አለቃ መቋሚያቸውን አነሱ፣ ተክሌ ዘንጉን አመጣ፣ ሁለቱም በቀኝ እጃቸው ተመረኮዙ፣ ግራ እጃቸውን እንደ ጸናጽል ሸረቡ፣ ፊትና ፊት ሆኑ። በዝማሜ ጀምረው፣ ንዑስ መረግድ አስከትለው፣ ድርብ መረግዱ ላይ ደረሱ። የሠሎሞንን ምቅናይ እያዜሙ…./
ገብረ ሐና፡- እኧኧኧእ…… ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ከናፍሪሁ ጽጌ ከናፍሪሁ ጽጌ እለ ያውኀዛ ከርቤ እኧኧኧእ… ከርሡ ሰሌዳ ከመ ቀርነ ኔጌ። …. እኧኧኧኧኧኧኧእ……
|
| |