ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ስነ ጽሑፍ

ወግ


ተዘረፍኩ

Read in PDF 2017-11-27 በታደለ አያሌው

በህይወቴ ደርሶብኝ የማያውቅ ዝርፊያ ትናንት ተዘረፍኩ፡፡ እንዲያውም አትበድ ቢለኝ እንጂ ሁኔታው ጨርቅ የሚያስጥል ነበር፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማታ ተማሪ ነኝ፡፡ ከትምህርት መልስ እያመነታሁ ወደ ላፍቶ ሞል ብቅ ብዬ ነበር፡፡ ወደ ጌም ዞኑ ሳንዣብብ አንድ ልጅ የእጅ ምልክት ሰጠኝ፡፡ ‹ና ፑል እንጫወት› ማለቱ መሰለኝ፡፡ ሄድኩለት፡፡ ሄኖክ እንደሚባል ነገሮኝ የሚያጫውተው ሰው ይጠብቅ እንደነበር ገለጸልኝ፡፡ ፍጥነቱ አይጣል ነው መቼም፡፡ በአንድ ደቂቃ ጓደኛሞች ሆንን፡፡ እፍ አልን በቅጽበት፡፡ ጨዋታ ጀመርን፡፡ በጨዋታው መሀል እየደጋገመ እንዲህ ይለኝ ነበር፡፡
‹‹አንተ እንዲያውም ትችላለህ፡፡ ኧረ ስንት አለ መሰለህ የኳስ ቁጥር ሁላ የማያውቅ፡፡ አሁን ትናንትና አንዱን ሶማሌ አምስት ሺ ብር ቆረጠምኩት እኮ ነው የምልህ››
‹‹እንዴት?›› እኔ ነኝ እንዴት ባዩ፡፡
‹‹አስይዘን ስንጫወት ነዋ፡፡ ብታይ እኮ ምንም አይችልም፡፡ ጣፍጦኛል፡፡ ዛሬ ራሱ እሱን እየጠበቅሁ ነው፡፡ ቅድም እዚያ አካባቢ እኮ ከጓደኛው ጋር አይቼው ነበር፡፡ በመጣልኝ፡፡ ዶላር እዚህ ድረስ ነው የያዘ፡፡››
ፑልን ሄኖክ ብቻ ይጫወታት! ዘንግ አያያዝ እንደሱ የሚያምርበት ሰው ይኖር ይሆን? ይራቀቅበታል፡፡ ከቆይታ በኋላ ልክ ጨዋታው ሊያልቅ ሲል ሶማሌ የተባለው ሰው መጣ፡፡ አነጋገሩ፣ ከንፈሩ፣ አኳኋኑ ሁሉ በርግጥም የሶማሌዎች አይነት ነው፡፡ እኔ ደግሞ ጥሎብኝ የምስራቅ ሰዎችን እወዳለሁ፡፡ አማርኛቸው ይጣፍጠኛል፡፡
‹‹እ ኦርያ›› አለው ሄኖክ፡፡
‹‹እ››
‹‹እንጫወት?››
‹‹መቶ አስር ነጥብ ትሰጠኛለህ?›› አለ ኦርያ እያስወደደው፡፡ ንግግሩን እኔ ስረዳው እንዲህ ሆነ እንጂ አባባሉ እንደ አባይ መንገድ ወደዚያም ወደዚህም ነው፡፡
‹‹መቶ አስር? መቶ አስር ብዙ ነው፡፡ እንደ ትናንቱ ግን መቶ ልስጥህ?››
‹‹አልጫወትም!›› መንገድ ጀመረ፡፡
‹‹እሺሺ ና፡፡ ና እሺ›› እየቀፈፈኝ ብሩን እኔ ያዝኩላቸው፡፡ ኳስ ወጣላቸውና ጨዋታ ጀመሩ፡፡ ሶማሌው ፑል ገና እየለመደ ነው፡፡ አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን ዘንግ አያያዙ በራሱ ተጨማሪ ያንብቡ


1 ከ 4

ከዚህ ቀደም ከቀረቡ ወጎች እና ሌሎች መካከል
ተዘረፍኩ
ታደለ አያሌው Read in PDF

በህይወቴ ደርሶብኝ የማያውቅ ዝርፊያ ትናንት ተዘረፍኩ፡፡ እንዲያውም አትበድ ቢለኝ እንጂ ሁኔታው ጨርቅ የሚያስጥል ነበር፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማታ ተጨማሪ ያንብቡ


‹ውጭ ሳሉ ከኛ፣ ውስጥ ሲገቡ ከነሱ›
ላሌ ይኸነው Read in PDF

አንድ ያልዘፈነ ዘፋኝ እንደሚከተለው አምቧቀሰ፡፡
‹‹ልጅ ሆነን ከወንድሞቼ ጋር ለጉድ እንበሻሸቅ ነበር፡፡ እናታችን ምሳችንን ታኖርልንና ወደ ሰንበቴ ትሄዳለች፡፡ ከዚያ እኛ ተጨማሪ ያንብቡ


ግብዣ

የግል ጽሑፍዎን ወደ ቤታችን ለመላክ እዚህ ይጫኑ

መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts