አንድ ያልዘፈነ ዘፋኝ እንደሚከተለው አምቧቀሰ፡፡ ‹‹ልጅ ሆነን ከወንድሞቼ ጋር ለጉድ እንበሻሸቅ ነበር፡፡ እናታችን ምሳችንን ታኖርልንና ወደ ሰንበቴ ትሄዳለች፡፡ ከዚያ እኛ እጃችንን ልንታጠብ ተማምለን እንወጣለን፡፡ ከመካከላችን አንዱ አዘናግቶን ይንደረደርና ወደ ቤት ገብቶ ቤቱን በውስጥ ይዘጋዋል፡፡ ብቻውን ሊበላ፡፡ እኛም እያባበልነው በሩን እንቆፈቁፋለን፡፡ እናባብለዋለን፡፡ እንለምነዋለን፡፡ እናስፈራራዋለን፡፡ ‹‹ኧረ ተው ግን ተው?›› እንለዋለን፡፡ የባሰበት እንደምንም ጥርሱን ነክሶ፣ ጅማቱ እስኪወጣ ገፍቶ ይገባል፡፡ ከዚያ እሱም ከኛ ወገን እንዳልነበር ይሆናል፡፡ ተጋግዘው በሩን በውስጥ ያጠብቃሉ፡፡ እንደገና ሁለቱን እናባብላለን፡፡ እንደገና እንለማመጣለን፡፡ እነሱን እንታገላለን፡፡ ላይከፍቱልን ነገር፡፡ ውጭ ሳለን አብሮ እንዳልራበን ወስጥ ሲገቡ ይክዱናል፡፡ … ያኔ ያለው ረሃብ! ብስጭቱ! እልሁ! … እናም ብሶቱ የጋለበትና ጉልበቱ የጠናለት እንደምንም ፏጭሮ ይገባና እኛን ክዶ ከቀደሙት እንዳንዱ ይሆናል፡፡ ቀሪዎቻችን እንዲሁ ጦም እንውላለን፡፡›› ይኸው ዘፍኖ የማያውቀው ዘፋኝ ከዚያ እስካሁን በሩ ላይ ቆሟል፡፡ ያንኳኳል የሚከፍትለት፣ ይገፋል የሚሸነፍለት፣ ያባብላል የሚራራለት፣ ይጮሃል የሚሰማው የለም፡፡ የቀደሙት ዘግተውትበት በሩ ላይ ነው ይኸው፡፡ እና ጉበኑን አንቆ ታንቆ ሊሞት! ምኞቱ ዘፋኝ መሆን፣ ኑሮው የቀደሙትን መማጠን፡፡ ጉበኑን ቢከፍቱለት፣ ከነሱ ይልቅ ሊዘፍን ይመኛል፡፡ እና ቀድመው አንድም ተፍጨርጭረው አንድም እንደዋዛ የገቡት በሩን በውስጥ አጥብቀው ዘግተውበታል፡፡ ወይ ዘፍነው የልብ አያደርሱ፣ ወይ በሩን ከፍተው ተቀባይ አያስገቡ እንዲያው ሲያሳዝን! ወይ እዚሁ ሲጠብቅ መሞቱ ነው፤ ወይ እንሱ እንደገቡት ለመግባት ጅማቱ መውጣቱ ነው፡፡ ምስኪን የኔብጤ? ለነገሩ እሱ ብቻ አይደለም መግቢያ ያጣ፡፡ ገዢው እንትን የቋመጡ እንትኖችን እንዲህ ዘግቶባቸዋል፡፡ በመከራ ተማርን እሚሉ መምህራን ተማሪዎች ላይ እንዲህ ዘግተዋል፡፡ በመከራ የታወቁ ደራስያን በጀማሪዎቹ ላይ እንዲህ ተጨማሪ ያንብቡ
በህይወቴ ደርሶብኝ የማያውቅ ዝርፊያ ትናንት ተዘረፍኩ፡፡ እንዲያውም አትበድ ቢለኝ እንጂ ሁኔታው ጨርቅ የሚያስጥል ነበር፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማታ ተጨማሪ ያንብቡ
አንድ ያልዘፈነ ዘፋኝ እንደሚከተለው አምቧቀሰ፡፡ ‹‹ልጅ ሆነን ከወንድሞቼ ጋር ለጉድ እንበሻሸቅ ነበር፡፡ እናታችን ምሳችንን ታኖርልንና ወደ ሰንበቴ ትሄዳለች፡፡ ከዚያ እኛ ተጨማሪ ያንብቡ
የግል ጽሑፍዎን ወደ ቤታችን ለመላክ እዚህ ይጫኑ
ለገሀር፣ አዲስ አበባ
19686
yehaarts@gmail.com
+251 912 944937
“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።
(2015-2024) © yehaarts