ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ሕይወት ተፈራ

“ማማ በሰማይ” እና ሌሎች መጽሐፍት ደራሲ

ሕይወት ተፈራ

[የትዉልድ ቀን] 0000-00-00
[አጭር መግለጫ]

ሕይወት ተፈራ ተወልዳ ያደገችዉ ሀረር ከተማ ነዉ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለች ጀምራ፣ በፖለቲካ ነክ እንቅስቃሴዎች ስትሳተፍ የኖረች ሲሆን፣ በዚህም የኢህአፓ ሁለተኛ ዋና ሰዉ ከሚባለዉ ጌታቸዉ ማሩ ጋር የፍቅር ግንኙነት እንድትመሰርት መንገድ ሆኗታል፡፡ ከጌታቸዉ ጋር የነበራት የፍቅር ግንኙነት ያን ያህል እድሜ ባይኖረዉም፣ ከእሱ ጋር ታሪክ የምትጋራበትን የዚያን ትዉልድ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከራሷ ዉጣ ዉረዶች ጋር ጨምራ ለኅትመት ያበቃችዉ “Tower in The Sky” የሚለዉ መጽሐፏ በብዙዎች አስወደዳት፡፡ በመቀጠልም “Mine to Wine” ያለችዉን መጽሐፍ ይዛ ወደ አንበብያን ዘንድ ብቅ አለች፡፡ መጽሐፍቶቿን በእንግሊዘኛ ቋንቋ ጽፋ ለንባብ ካበቃች በኋላ በአማርኛ ቋንቋ እንዲተረጎሙ ስታደርግ የቆየችው ሕይወት ተፈራ በአዲሱ ስራዋ ለየት ያለ አካሄድ ተከትላለች። 248 ገጾች ያሉትን “ምንትዋብ” መጽሐፍ መጀመሪያዉኑም የጻፈችው በአማርኛ ነው።

[ከመጻሕፍቱ መካከል]
* ማማ በሰማይ

[መገኛዎቹ] አልተገለጸም (ወደ ፊት የሚካተት)
[ምንጮቻችን] ከልዩ ልዩ ቃለ ምልልስ


ስለሌሎች ደራስያን እዚህ ይወቁ

መጻሕፍት ከየምድባቸዉ ለመምረጥ እዚህ ይግቡ መጻሕፍት ከጠቅላላ ዝርዝር ለመምረጥ እዚህ ይግቡ
ሕይወት ተፈራ
መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts