ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ታደለ አያሌው

“ረበናት” እና ሌሎች መጽሐፍት ደራሲ

ታደለ አያሌው

[የትዉልድ ቀን] 1982-09-12
[አጭር መግለጫ]

የተወለደዉ በደብረ ማርቆስ ከተማ አቅራቢያ በምትገኝ የወቢ እነችፎ በምትባል የገጠር ቀበሌ ነዉ። የመጀመሪያ ዲግሪዉን ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ በኮምፒዉተር ሳይንስ፣ ኹለተኛ ዲግሪዉን በዚያዉ በኮምፒዉተር ሳይንስ (Networking and Security) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አግኝቷል። ተሥፋዬ አበበ (ፋዘር፣ ክ/ዶክተር) ባቋቋሙት የኪነ ጥበብ ማዕከል እና ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በተለያዩ ክበባት የስነ ጽሑፍ ሙያዉን እያሻሻለ ያደገ ሲሆን፣ ስነ/ኪነ-ጥበብ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ አጫጭር ስልጠናዎችንም ከተለያዩ ተቋማት ወስዷል። ባ/ዳር ዩኒቨርስቲ በ፳፻፬ዓ.ም ፕሮዱዩስ ባደረገው ‹ድብብቆሽ› ቴአትር ላይ፣ ፖሊ የኪነ ጥበባት ማዕከል ያዘጋጃቸው ጥቂት ቴአትሮች ላይ፣ በወርሀዊዉ የሙሉዓለም የባህል ማዕከልና በሌሎች መርኃ ግብራት በመሪነትና አጋዥ ተዋናይነትም ሰርቷል። ከዚህ ቀደም ረበናት (፳፻፲፩ዓ.ም) እና ገረገራ (፳፻፲፬ዓ.ም) የተባሉ ረዣዥም ልብ ወለዶች ለኅትመት የበቁለት ሲሆን፣ ሸምጋይ የተባለ የሙሉ ጊዜ ተዉኔት ደግሞ በብሔራዊ ቴአትር ሊመደረክ ወረፋ እየጠበቀ ይገኛል። በተጨማሪም፣ የዚህ ድረ ገጽ (የሓ ቤተ ጥበብ) ባለቤት ነዉ።

[ከመጻሕፍቱ መካከል]
* ረበናት
* ገረገራ

[መገኛዎቹ] ፌስቡክ፡ - https://facebook.com/tadele.yehaarts ኢ-ሜይል፡ - info@yehaarts.com
[ምንጮቻችን] https://yehaarts.com


ስለሌሎች ደራስያን እዚህ ይወቁ

መጻሕፍት ከየምድባቸዉ ለመምረጥ እዚህ ይግቡ መጻሕፍት ከጠቅላላ ዝርዝር ለመምረጥ እዚህ ይግቡ
ታደለ አያሌው
መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts