ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ዳንኤል ክብረት

“ስማችሁ የለም እና ሌሎች” እና ሌሎች መጽሐፍት ደራሲ

ዳንኤል ክብረት

[የትዉልድ ቀን] 0000-00-00
[አጭር መግለጫ]

ከሃያ ዓመታት በላይ ወደ ሠላሳ የሚደርሱ መጻሕፍት በግሉ እና ከሌሎች ሰዎች ጋር በትብብር ለንባብ ያበቃዉ ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፣ በአሁኑ ሰዓት የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ እና የተወካዮች ምክር ቤት አባል ነዉ፡፡ በታላቁ ማኅበር፣ ማኅበረ ቅዱሳን ምስረታ ከፍተኛ ሚና እንደነበረዉ የሚታወቅለት ዲ/ን ዳንኤል፣ እጅግ አነጋጋዊ በሆኑ ጽሑፎቹ እና ንግገሮቹ ይታወቃል፡፡ ቀደም ብሎ በሃይማኖት ሰባኪነቱ፣ ጎን ለጎን ደግሞ መንፈሳዊ መጻሕፍት (“የበርሓ አባቶች”፣ “የቤተ ክርስቲያን መረጃዎች”፣ “የመጽሐፍ ቅዱስ ሀገሮች”፣ “ራዕየ ዮሐንስ”፣ “አራቱ ኃያላን”፣ “ቬነሲያና ሌሎች”፣ “ከሰይጣን ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ”፣ “እጨጌ እንባቆም”፣ “ኢትዮጵያዊዉ ሱረራፊ” እና ሌሎች)፣ ባለፉት ዐሥር ዓመታት ደግሞ ማኅበራዊ ትችቶችን መነሻ ያደረጉ እይታዎቹን በግሉ ድረ-ገጽ እና በልዩ ልዩ መጽሔቶች/ጋዜጦች ሲያስነብብ ቆይቷል፡፡ እነዚህን ማኅበራዊ ተኮር እይታዎቹንም እያሰባሰበ ወደ ኅትመት ያበቃቸዉ ሲሆን፣ “የሁለት ሐዉልቶች ወግ”፣ “ጠጠሮቹ እና ሌሎች”፣ “የኔ ጀግና”፣ “እኛ የመጨረሻዎቹ”፣ “ስማችሁ የለም”፣ እና ሌሎች ይጠቀሱለታል፡፡

[ከመጻሕፍቱ መካከል]
* ስማችሁ የለም እና ሌሎች
* ኑ! ሀገሬን እናዋልዳት እና ሌሎች
* የኔ ጀግና እና ሌሎች
* የአዲስ አበባ ውሾች
* ብቻዬን እቆማለሁ እና ሌሎች
* ራእየ ዮሐንስ
* ኢትዮጵያዊው ሱራፊ
* የሌለውን ፈላስፋ ፍለጋ እና ሌሎች
* የሰርቆ አደሮች ስብሰባ እና ሌሎች
* እኛ የመጨረሻዎቹ እና ሌሎች

[መገኛዎቹ] http://www.danielkibret.com
[ምንጮቻችን] ከልዩ ልዩ ቃለ ምልልስ


ስለሌሎች ደራስያን እዚህ ይወቁ

መጻሕፍት ከየምድባቸዉ ለመምረጥ እዚህ ይግቡ መጻሕፍት ከጠቅላላ ዝርዝር ለመምረጥ እዚህ ይግቡ
ዳንኤል ክብረት
መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts