ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
እንዳለጌታ ከበደ

“በዓሉ ግርማ ሕይወቱና ሥራዎቹ” እና ሌሎች መጽሐፍት ደራሲ

እንዳለጌታ ከበደ

[የትዉልድ ቀን] 0000-00-00
[አጭር መግለጫ]

የብዕሩ ማህፀን የወለዳቸው በርካታ ሥራዎችን ለአንባቢያን አድርሷል። ያለስስት ይጽፋል። ያለ ድካም ጥናትና ምርምር ያደርጋል። 13 ረጅምና አጫጭር ልብወልድ፣ ኢ ልብወለድና የግጥም መጽሐፍትን አሳትሞ ለንባብ አብቅቷል። ጥናትና ምርምርን መሠረት አድርጎ ያዘጋጃቸው መጽሐፍቱ እንደተደከመባቸው የሚያስታውቁ ናቸው ተብሎ ተመስግኗል። በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ጽሑፎችንም ለተለያዩ የህትመት መገናኛ ብዙኃን በየወቅቱ ያጋራል። በቅርቡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፎክሎር ሦስተኛ ዲግሪውንም አግኝቷል። አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ባልተለመደ መልኩ ዛጎል የተሰኘ የመጽሐፋት ባንክን መስርቷል - ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ (ዶ/ር)። መጽሐፍትን ሰብስቦ ለማረሚያ ቤቶችና ትምህርት ቤቶች ማሰራጨት የሚታወቅበት ተግባሩ ነው።

[ከመጻሕፍቱ መካከል]
* በዓሉ ግርማ ሕይወቱና ሥራዎቹ
* ጽላሎት
* ምሳሌ
* ያልተቀበልናቸው
* እምቢታ የቃቄ ወርድወት
* ዛጎል
* የመኝታ ቤት ምስጢሮች

[መገኛዎቹ] ፌስቡክ፡ - https://facebook.com/1420543384894038/
[ምንጮቻችን] https://www.bbc.com/amharic/news-58176596


ስለሌሎች ደራስያን እዚህ ይወቁ

መጻሕፍት ከየምድባቸዉ ለመምረጥ እዚህ ይግቡ መጻሕፍት ከጠቅላላ ዝርዝር ለመምረጥ እዚህ ይግቡ
እንዳለጌታ ከበደ
መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts