ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ስብሀት ገብረእግዚአብሄር

“ትኩሳት ፡ እንደ ወረደ” እና ሌሎች መጽሐፍት ደራሲ

ስብሀት ገብረእግዚአብሄር

[የትዉልድ ቀን] 0000-00-00
[አጭር መግለጫ]

ስብሃትን በማድነቅ የሚከተሉት ሁሉ በሱ እጅ ጽሑፍ የሚከተበውን ስብሃትለአብ የሚለውን ስሙን አንብበዋል፡፡ ገና በልጅነቱ አዲስ አበባ ሲመጣ ስሙን ቢያሳጥረውም አባቱ መምሬ ገብረእግዚአብሔር ገብረዮሐንስ እና እናቱ ወይዘሮ መዓዛ ተወልደመድህን ያወጡለት ስም ስብሃትለአብ ገብረእግዚአብሔር የሚል ነው፡፡ ስብሃት ለአብ “ወለላይ” የሚላቸው እናቱ እና አባቱ አቦይ ገብረእግዚአብሔር ከበፊት ትዳሮቻቸው ያፈሯቸውን ጨምሮ በአጠቃላይ 13 ልጆች ወልደዋል፡፡
ደራሲ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር፣ ከበርካታ የፈጠራ ስራዎቹ በመፃሕፍ ከታተሙለት መካከል “አምስት ስድስት ሰባት” እና ከሌሎች አስር አጭር ልቦለዶች ጋር በ1981፣ “ትኩሳት” ረዥም ልቦለድ በ1990፣ “ሌቱም አይነጋልኝ” ረዥም ልቦለድ በ1992፣ “ሰባተኛው መላክ” ረዥም ልቦለድ በ1992 “እግረ መንገድ” ቁጥር ፩ ከ1985 እስከ 1990 በጋዜጣ ከተፃፉ ሥራዎች የተሰበሰበ፣ “እግረ መንገድ” ቁጥር ፪ ከ1985 እስከ 1990 በጋዜጣ ከተፃፉ ሥራዎች የተቀነጨበ፣ “እነሆ ጀግና” በ1997 እና “የፍቅር ሻማዎች” ሲሆኑ “ዛዚ” የትርጉም ሥራ ነው፡፡ ከስብሃት የድርሰት ሥራዎች ውስጥ “ሌቱም አይነጋልኝ” ወደ ፈረንሳይኛ ተተርጉሞ ለፈረንሳይኛ አንባቢዎች ሊቀርብ ችሏል፡፡

[ከመጻሕፍቱ መካከል]
* እነሆ ጀግና!
* ቦርጨቅ
* ሌቱም አይነጋልኝ
* ትኩሳት ፡ እንደ ወረደ

[መገኛዎቹ] የለም(Not Applicable)
[ምንጮቻችን] www.addisadmassnews.com


ስለሌሎች ደራስያን እዚህ ይወቁ

መጻሕፍት ከየምድባቸዉ ለመምረጥ እዚህ ይግቡ መጻሕፍት ከጠቅላላ ዝርዝር ለመምረጥ እዚህ ይግቡ
ስብሀት ገብረእግዚአብሄር
መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts