ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
በዓሉ ግርማ

“ኦሮማይ” እና ሌሎች መጽሐፍት ደራሲ

በዓሉ ግርማ

[የትዉልድ ቀን] 0000-00-00
[አጭር መግለጫ]

“ከአድማስ ባሻገር”፣ “የኅሊና ደወል”፣ “የቀይ ኮከብ ጥሪ”፣ “ሐዲስ”፣ “ደራሲው” እና “ኦሮማይ” በሚሉት ታላላቅ መጻሕፍት የሚታወቁት ደራሲ በዓሉ ግርማ፣ በኢላባቡር ክፍለ ሀገር ሱጴ በምትባል ሥፍራ በ1928 ዓ.ም. ተወለዱ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በልዕልት ዘነበወርቅ ትምሕርት ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት አጠናቀዋል። ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖሊቲካል ሳይንስ እና ኢንተርናሽናል ሪሌሽንስ የቢ.ኤ. ዲግሪ ያገኙ ሲሆን፤ በዚሁ ተመሳሳይ መስክ ከአውሮፓ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
በተለይ በልብ ወለድ እና በፈጠራ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ከታወቁት የኢትዮጵያ የዘመኑ ደራሲዎች መካከል ተወዳጅነትና ዝናን ያተረፉ ዕውቅ ደራሲ ነበሩ። ከጻፏቸው በርካታ ድርሰቶቻቸው ውስጥ «ከአድማስ ባሻገር» የተሰኘው መጽሐፋቸው በሩስኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በቀድሞዋ የሶቪየት ሶሽያሊስት ሪፑብሊኮች ኅብረት ቀርቧል። በተጨማሪም በጋዜጠኝነት ሙያም ስማቸውን ያስጠሩ፤ ሙያቸውንም ያስከበሩ ደራሲ ነበሩ። «የዛሬይቱ ኢትዮጵያ» ጋዜጣ፤ የመነን መጽሔት፤ የአዲስ ረፖርተር መጽሔት፤ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ከመሥራታቸውም ባሻገር፤ ብዙ ወጣት ጋዜጦችን ለማፍራት ጥረት አድርገዋል። አዲስ ሪፖርተር የተባለውን መጽሔትም ደረጃው ከፍ እንዲልና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲገመገም አድርገዋል። በጋዜጠኝነት ሙያቸው በኢትዮጵያ ራዲዮ ሠርተዋል።
ደራሲ በዓሉ ግርማ ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱና ብዙ ሥራዎችን ያቀረቡ ሲሆን፤ የመጨረሻው መጽሐፋቸው «ኦሮማይ» በመባል ይታወቃል። ይኼውም መጽሐፍ በወቅቱ በነበረው የደርግ መንግሥት ሊደገፍ ባለመቻሉ በ1976 ዓ.ም. ለደራሲው ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሊሆን በቅቷል።

[ከመጻሕፍቱ መካከል]
* ደራሲው
* ከአድማስ ባሻገር
* ኦሮማይ
* የቀይ ኮከብ ጥሪ

[መገኛዎቹ] የለም(Not Applicable)
[ምንጮቻችን] https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A0%E1%8B%93%E


ስለሌሎች ደራስያን እዚህ ይወቁ

መጻሕፍት ከየምድባቸዉ ለመምረጥ እዚህ ይግቡ መጻሕፍት ከጠቅላላ ዝርዝር ለመምረጥ እዚህ ይግቡ
በዓሉ ግርማ
መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts