ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ዓለማየሁ ገላጋይ

“ውልብታ” እና ሌሎች መጽሐፍት ደራሲ

ዓለማየሁ ገላጋይ

[የትዉልድ ቀን] 0000-00-00
[አጭር መግለጫ]

ዓለማየሁ ገላጋይ በ1960 ዓ.ም በአራት ኪሎ አካባቢ ተወለደ። በዳግማዊ ምኒልክ ፩ኛ ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምሯል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስኩል ኦፍ ጆርናሊዝም ተምሮ ተመርቋል። ዓለማየሁ ገላጋይ "ኔሽን" ፣ "አዲስ አድማስ" ፣ "ፍትሕ" ፣ "አዲስ ታይምስ" ፣ እና "ፋክት"ን ጨምሮ በተለያዩ ጋዜጦችና መጽሔቶች ላይ በሚያቀርባቸው መጣጥፎች ይታወቃል። ከሥራዎቹ መካከል፡ "ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት"፣ "ቅበላ"፣ "የብርሃን ፈለጎች"፣ "ኢህአዴግን እከሳለሁ"፣ "ኩርቢት"፣ "ወሪሳ"፣ "አጥቢያ"፣ "የፍልስፍና አፅናፍ"፣ "በፍቅር ስም"፣ "መለያየት ሞት ነው"፣ "በእውነት ስም (ታለ)"፣ "ውልብታ" እና "በእምነት ሥም(ሐሰተኛው)" የተሰኙ ልቦለድና ኢልቦለድ መጻሕፍት ለአንባቢያን አበርክቷል። ከዚህ በተጨማሪም "መልክዓ–ስብሐት" በተሰኘው መጽሐፍ 27 ጸሐፊያንያን ደራሲያን፣ ገጣሚያንና ሰዓሊያን አሳትፎ በማሰናዳት ለአንባብያን አድርሷል።
ዓለማየሁ ገላጋይ በሃያሲነትም ስም ያተረፈ የብዕር ሰው ነው። ገና ለሕትመት ያልበቁ በርካታ ሥራዎችም አሉት።

[ከመጻሕፍቱ መካከል]
* ውልብታ
* ታለ በዕውነት ሥም
* በፍቅር ሥም
* ወሪሳ
* ሐሰተኛው
* አጥቢያ
* ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት

[መገኛዎቹ] ፌስቡክ፡ - https://facebook.com/alemayhugelagay
[ምንጮቻችን] https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%93%E1%88%88%E


ስለሌሎች ደራስያን እዚህ ይወቁ

መጻሕፍት ከየምድባቸዉ ለመምረጥ እዚህ ይግቡ መጻሕፍት ከጠቅላላ ዝርዝር ለመምረጥ እዚህ ይግቡ
ዓለማየሁ ገላጋይ
መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts