ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ዘነበ ወላ

“የምድራችን ጀግና” እና ሌሎች መጽሐፍት ደራሲ

ዘነበ ወላ

[የትዉልድ ቀን] 0000-00-00
[አጭር መግለጫ]

“ማንበብና መጻፍ ነዉ ሱሴ፤ ሌትም ቀንም አልመርጥም፡፡ የምተኛዉ ረጅም እንቅልፍ ከአራት ሰዓት አይበልጥም፡፡ ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ቢኖረኝ ብዬ ተመኝቼ አላዉቅም፣ ቢኖረኝ ግን በሁሉም ክልሎች ዘመናዊ ቤተ መጻሕፍት አስገነባለሁ፡፡ ‹አንብብ-አንብቢ-አንብቡ-እናንብብ› በሚል መርህ ትዉልዱን ማነጽ ተግባሬ ይሆን ነበር” የሚለዉ ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ፣ ተወልዶ ያደገዉ አዲስ አበባ፣ ጨርቆስ የሚባለዉ አካባቢ ነዉ፡፡ በተለይም የሁሉንም የልጅነት ሕይወት ባነሳሳበትና፣ “ልጅነት” በተባለዉ መጽሐፉ ከልጅ እስከ አዋቂዎች ድረስ የሚታወቅ ሲሆን፣ ጨመር ያሉ ተወዳጅ መጻሕፍት አሉት፡፡ ከእነዚህም መካከል የደራሲ ስብሐትን ሕይወትና ፍልስፍና በተመለከተ የጻፈዉ “ማስታዎሻ” በሚል፣ የታላቁን ሳይንቲስት የተወልደ ገ/እግዚአብሔርን ረዥም የህይወት ከፍ-ዝቅ የመዘገበበት “የምድራችን ጀግና” በሚል፣ የራሱን የባህረኛነት ተሞክሮ ያጋራበት “መልህቅ”በሚል እና ሌሎቹም መጻሕፍት ይጠቀሱለታል፡፡

[ከመጻሕፍቱ መካከል]
* ማስታወሻ
* የምድራችን ጀግና
* ልጅነት

[መገኛዎቹ] ፌስቡክ፡ - https://facebook.com/100397128540020/
[ምንጮቻችን] ከልዩ ልዩ ቃለ ምልልስ


ስለሌሎች ደራስያን እዚህ ይወቁ

መጻሕፍት ከየምድባቸዉ ለመምረጥ እዚህ ይግቡ መጻሕፍት ከጠቅላላ ዝርዝር ለመምረጥ እዚህ ይግቡ
ዘነበ ወላ
መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts