ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ተክሉ ጥላሁን

“የጭን ቁስል” እና ሌሎች መጽሐፍት ደራሲ

ተክሉ ጥላሁን

[የትዉልድ ቀን] 1970-05-12
[አጭር መግለጫ]

ደራሲ እና አዘጋጅ ተክሉ ጥለሁን ተወልዶ ያደገዉ በአዲስ አበባ ነዉ፡፡ ከትምህርት ቤት ጀምሮ በሚኒሚዲያ እና በተለያዩ አጋጣሚዎች በንቃት እየተሳተፈ ያደገ ሲሆን፣ መደበኛ ስልጠናዉንም በጋዜጠኝነት አግኝቷል፡፡ “ያልሰከነ ዜማ” የመጀመሪያዉ የታተመ መጽሐፉ ሲሆን፤ ከ27 ጊዜ በላይ ታትሞ በሰፊዉ የተነበበለትንና፣ በእዉነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የጻፈዉን “የጭን ቁስል”ን ጨምሮ “የሎጥ መንገድ”፣ “ከስኬት በስተጀርባ”፣ “የስኬት መንገዶች”፣ “ዴዝዴራታ”፣ “የቀን ጨለማ” እና ሌሎች መጽሐፍትን ለኅትመት ብርሐን አብቅቷል፡፡ ለብቻዉ እና ከሌሎች ጋር በመጣመር የጻፋቸዉ እና ያሳተማቸዉ መጽሐፍትም ቀላል የሚባሉ አይደሉም፡፡ ለምሣሌ፡ “ጃንሆይን ማን ገደላቸዉ?” (ከዐቢይ ደምሴና ተሥፋሁን ምትኩ ጋር)፣ “ያልተዘመረላቸዉ” (በአሜሪካ ኤምባሲ ትብብር) ይጠቀሱለታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከስድስት በላይ በሆኑ የአማርኛ ፊልሞች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያለዉ ሲሆን (“ዐሥርቱ ቀናት”፣ “እፉዬ ገላ”፣ “አብሳላት” እና ሌሎች)፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በዉጭ ሀገር ቋንቋ የተጻፉ ልዩ ልዩ ቅርጽ ያላቸዉ መጽሐፍትን ወደ አማርኛ ቋንቋ በመመለስ ሂደቱ ላይ ሰፊና ቀጥተኛ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል፡፡

[ከመጻሕፍቱ መካከል]
* የጭን ቁስል

[መገኛዎቹ] ፌስቡክ፡ - https://facebook.com/teklu.tilahun ቴሌግራም፡ - https://t.me/teklu_tilahun
[ምንጮቻችን] https://yehaarts.com


ስለሌሎች ደራስያን እዚህ ይወቁ

መጻሕፍት ከየምድባቸዉ ለመምረጥ እዚህ ይግቡ መጻሕፍት ከጠቅላላ ዝርዝር ለመምረጥ እዚህ ይግቡ
ተክሉ ጥላሁን
መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts