ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ኃይለ መለኮት መዋዕል

“ጉንጉን” እና ሌሎች መጽሐፍት ደራሲ

ኃይለ መለኮት መዋዕል

[የትዉልድ ቀን] 1943-10-16
[አጭር መግለጫ]

የተወለደዉ በሰሜን ሸዋ ይፋት ኣውራጃ ማጀቴ በተባለች አነስተኛ ከተማ ነዉ። ደቡብ ኮምቦልቻ ላይ ፊደል ከቆጠረ እና ዳዊት ከደገመ በኋላ የኣንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በቀድሞ የኤርትራ ክ/ሀገር ኣሥመራ ከተማ ኣክሪያ ት/ቤት ተከታተለ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም እዚያው ኣሥመራ ልዑል መኮንን መታበቢያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አጠናቀቀ፥ በመምህርነት ሙያም ሰለጥኖ ኣገልግሏል።
ጋሽ ኃይለመለኮትን ስናስብ ከማንረሳቸዉ መጻሕፍት መካከል “የወዲያነሽ” (ረዥም ልቦለድ፣ በ1978ዓ.ም) ፣ “ጉንጉን” (ረዥም ልቦለድ፣ በ1982ዓ.ም) ፣ “እንካሰላምታ” (በ2005ዓ.ም) ፣ “ኦቴሎ” (ትግርኛ፣ 2007ዓ.ም) ይጠቀሳሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በየመድረኩ የሚያቀርባቸዉ ዲስኩሮች እና ምክሮች እንዳሉ ሆነ እሱ አርትዖት ያልሰራለት የሀገራችን ደራሲ መኖሩን እንጠራጠራለን፡፡ በተለይ አሁን አሁን፣ የጀማሪና ነባር ደራስያንን ስራ እያየ እርማት መስጠቱን ሥራዬ ብሎ ተያይዞታል፡፡

[ከመጻሕፍቱ መካከል]
* ጉንጉን

[መገኛዎቹ] ፌስቡክ፡ - https://facebook.com/
[ምንጮቻችን] https://facebook.com/getu.temesgen


ስለሌሎች ደራስያን እዚህ ይወቁ

መጻሕፍት ከየምድባቸዉ ለመምረጥ እዚህ ይግቡ መጻሕፍት ከጠቅላላ ዝርዝር ለመምረጥ እዚህ ይግቡ
ኃይለ መለኮት መዋዕል
መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts