ገረገራ
[ርዕሥ] | ገረገራ |
[ደራሲ] | ታደለ አያሌው |
[አርታዒ] | ኃይለ መለኮት መዋዕል |
[ምድብ] | ልብ ወለድ |
[ዘዉግ] | ስለላ፣ ሴራና ምስጢራዊ |
[አሳታሚ] | የሓ ቤተ ጥበብ |
[የመጀ.ዕትም] | 2014-07-10 |
[አሁን የደረሰበት] | 1ኛ ዕትም |
[ISBN (መለያ)] | 978-99944-3-533-3 |
[የገጽ ብዛት] | 244 |
[የሽፋን ዋጋ] | 180 |
[መሸጫ ዋጋ] | 150 |
| |
[ቅንጭብ]
ብቻ አትቀደሚ! አንዴ አይቅደሙሽ እንጂ፣ ከተቀደምሽ አንቺን ለመድፈቅ የማይበረታ የለም። ሳር ቅጠሉ ይነሳብሻል። ምናምንቴዉ ሁሉ ጎሮሮሽ ላይ ይቆማል። እንኳንስ የኔ ነዉ የምትዪዉ ይቅርና፣ ራሳቸዉ ያንቺ ነዉ ያሉሽን እንኳን ይወስዱብሻል። ጭራሽ ባዶሽን ማስቀረታቸዉም አልበቃ ብሏቸዉ፣ ወሰደችብን ብለዉ ያዋክቡሻል። መልሰዉ ደግሞ ይዘባበቱብሻል። ይሸልሉብሻል። ግድየለም እነሱን ራሳቸዉን እንኳን አጥቻቸዉ የለ ብለሽ እንኳን እንዳትጽናኝ፣ የመጽናኛ ትንፋሽ የሚባል አያስቀሩልሽም። አንቺን በፍህም ያዉም በሹል ሚስማር ላይ አቁመዉሽ፣ ያሽካኩብሻል። ልንገርሽ? በፍጹም እንዳትቀደሚ። ወደ አንቺ የተዘረጋዉ እጅ ለፍቅርም ይሁን ለጸብ፣ እንዳመጣጡ አፈፍ አድርጊዉ እንጂ አትቀደሚ። ለምንም ነገር፣ ማንም አይቅደምሽ! የፈለገ ምን ብትሸሸዉ፣ ዉጊያዉ እንደሆነ አይቀርልሽም እንግዲህ! ይልቁንስ ምረጪ። መዋጋት ያለብሽ ራስሽን ለማዳን ነዉ ወይስ ራሱን የሚዋጋሽን ቤተሰብ ለማትረፍ? ወጣ ወረደ፣ እንዳትቀደሚ!
[ታደለ አያሌው ሌሎች መጻሕፍት] * ረበናት
* ገረገራ
✓ እዚህ ላይ ይግዙት
ሌሎች መጻሕፍት ይምረጡ