፩) ትውልድ(ቀንና ቦታ)፣ ቤተሠብ፣ ትምህርት
የትዉልድ ቦታ፡ ሀረርጌ፣ ኢትዮጵያ
የትዉልድ ቀን፡ መስከረም ፲፯፣ ፲፱፻፳፱ዓ.ም.
የእረፍት ቀን፡ ታኅሣሥ ፯፣ ፳፻፲፫ዓ.ም.
ትምህርት፡ የቄስ ትምህርት (ሀረርጌ)፣ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት (ተፈሪ መኮነን፣ አዲስ አበባ)፣ ከፍተኛ ትምህርት (ኖርዝ ዌስተርን፣ አሜሪካ)
፪) ሙያ፣ አስተዋጽዖ፣ ተሰጥዖ
በኃላፊነት፡ በሦስቱም ቴአትር ቤቶች (ሀገር ፍቅር፣ ብሔራዊ፣ ባህል አዳራሽ)
በደራሲት፡ እቃዉ(ቴአትር)፣ መተከዣ (ልብወለድ መጽሐፍ)፣ የመጨረሻዉ መጀመርታ (ልብ ወለድ መጽሐፍ)፣ መልክአ ኡመር(ቴአትር - ትርጉም)፣ ኡመር ሃያም(ቴአትር - ትርጉም)፣ እና ሌሎችም፡፡
በአዘጋጅነት፡ የእሾህ አክሊል፣ ጠልፎ በኪሴ፣ የደካሞች ወጥመድ፣ ሮሚዮ እና ጁሊዬት፣ ማነዉ ኢትዮጵያዊ፣ ቴአትር ሲዳዳ፣ ሰሎሞን እና ሳባ፣ እቃዉ፣ የሺ፣ ተሐድሶ፣ መልክአ ኡመር፣ ሰኔ እና ሰኞ፣ አባት እና ልጅ፣ መንገደኞች እና ሌሎች፡፡
በተዋናይነት
ቴአትር፡ ሐምሌት(እንደ ሐምሌት)፣ ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት (እንደ ግራዚያኒ)፣ የድል አጥቢያ አርበኛ (እንደ ግራዚያኒ)፣ እቃዉ (እንደ ዶክተር)፣ መልክአ ኡመር (እንደ ኡመር ሀያም)፣ አሉላ አባ ነጋ
ፊልም፡ ገመና(የቴሊቪዥን ድራማ)፣ ሼፉ፣ አልማዜ፣ ዴዝዴሞና፣ ሀብትሽ በሀብቴ፣ ትዉልድ እና ሌሎቹም፡፡
በመምህርነት፡ በዋናነት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች፣ ክበባት (ለምሳሌ ተሥፋዬ አበበ ተጓዥ የቴአትር ክበብ)፣ በቴሌቪዥን (ስነ-ስኬት፣ በናሁ ቴሊቪዥን)
፫) መሰናክሎች፣ ማለፊያ ጥንካሬዎች
ያን ያህል ባይሆንም፣ የቆዳ ቀለሙ ለወጥ ማለቱ ዐይን ላይ ያስገባዉ ነበር፡፡ በዚያም ላይ አያቱ ቆለጭ፣ የተፈሪ መኮነን (በኋላ ዐጼ ኃይለ ሥላሴ) ሞግዚት ስለነበሩ፣ ከመኳንንት ወገን ነዉ፡፡ በመሆኑም በኋላ ደርግ በመጣ ጊዜ፣ የመሳፍንት እና የመኳንንት ወገኖችን እያደነ ሲያስር፣ እሱም ለእስር ተዳርጎ ነበር፡፡
፬) ተሥፋዬ ገሠሠን አጥተን እንዳናጣው ነገር
አንድ ቃል ነበረዉ። ሁልጊዜም በያመቱ ቢያንስ አንድ መጽሐፍ አሳትማለሁ የሚል። እንደቃሉም በዛ ያሉ መጽሐፍትን ከእድሜዉ እና ከንባቡ እየቀዳ እየሰጠን ነበር። የተቋረጠበትን ምክንያት በዉል ባናዉቀዉም፣ በቴሌቪዥን ጀምሮት የነበረዉ “ስነ ስኬት” የሚለዉ መርሐ ግብሩ እጅግ ጠቃሚ ነበር።
፭) መርሆች፣ የህይወት ፍልስፍናው
“የወፍ ወንዱ፣ የፖለቲከኛ ሆዱ አይታወቀምና ሁሉን በብልሀት ያዙ” የሚል ምክር ከአፋቸዉ አይጠፋም።
ምንጮቻችን
ልዩ ልዩ ቃለ ምልልሶች (ETV - አርሂቡ፣ ጨዋታ ከቴዲ ጋር፣ ድሬ ዩቱብ፣ EBS - ሰይፉ ሾዉ)
አስተያየት እዚህ ያስቀምጡልን
እስካሁን (0) አስተያየቶች ተሰጥተዉበታል
ለሁሉም ጊዜ አለዉ
ተሥፋዬ ገሠሠ
ከዚህ ቀደም ግለ ታሪካቸዉን ካቀረብንላቸዉ መካከል
የእኔን ሥራ የሚያዩ ሁሉ ተስፋ እንዲያገኙ፣ ስለኢትዮጵያ እና ስለ አፍሪቃ ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው፣ በፀሐይ ጮራ እንዲሞቁ፣ ከሁሉም በላይ ግን “ይቻላል” የሚል እምነት እንዲኖራቸው ፍላጎቴ ነውእጅግ የተከበሩ የዐለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ
Read in PDF
ሊቁ ልበ ሙሉ ነበሩ፡፡ ኃይማኖተኛና ‹ዛሬ ከጨለመብን ይልቅ ነገ የሚበራልን ይበልጣል› ባይ ተስፈኛም ነበሩ፡፡ ዋጋ ቢያስከፍላቸውም ራሳቸውን የሚያከብሩ ክቡር ሰው ነበሩ፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
ያለፈ ጥረታችንን፣ ሳስታምመው ትዝ ሲለኝ ከሞከርነው ነገር ይልቅ ያልሞከርነው ነው እሚቆጨኝ፡፡ብላቴን ጌታ ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን
Read in PDF
የማይድን በሽታ ሳክም
የማያድግ ችግኝ ሳርም
የሰው ሕይወት ስከረክም
እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም።
የጋሽ ጸጋዬን ህይወት ከዚህ በላይ የሚገልጸው ቃል የለም(አራት ተጨማሪ ያንብቡ
የአባቱ ልጅ፣ ቁርጠኛውና ኢትዮጵያዊውን ጸሐፌ ተውኔት፤ ለዚህ ዕትም መርጠንላችኋል፡፡መንግስቱ ለማ
Read in PDF
ምልከታው ከፊት ከአባቶቹ ዘመን፣ ከኋላ የልጆቹን ዘመን ያጠናቀረ ነበር፡፡ ዘመናዊነትን ይቀበላል፣ የአባቶቹን ባህል ግን አይተላለፍም ነበር፡፡ የህይወት አካሄዱን ልብ ብለን ያስተዋልን እነደሆነ፣ ፊት ለፊት ራሱን ለአደጋ የሚያጋፍጥ ሳይሆነ በጨዋታ እያስመሰለ የሚሸነቁጥ ዋዘኛ መሳይ ሰው ነበር፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
መልእክተ የሓ
በዚህኛዉ ዐምድ ታሪካቸዉ እንዲቀርብ የምትፈልጓቸዉን ሰዎች እንድትጠቁሙን ወይም ደግሞ የተጻፈ ታሪካቸዉ ካለዎ በዚህ በኩል ቢያገኙን ደስታዉን አንችለዉም፡፡