ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ግለ ታሪክ

የከባለ ተሞክሮ አንጋፋዎችና ወጣቶች ግለ ታሪክ

፩) ትውልድ(ቀንና ቦታ)፣ ቤተሠብ፣ ትምህርት

በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። በስጋ የተለዩት ደግሞ ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ነበር፡፡ ና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ተልከው በስመ ጥሩው የሎንዶን ዩኒቨርሲቲ የስሌድ ኪነ ጥበብ ማዕከል (Faculty of Fie Arts at Slade) የመጀመሪያው አፍሪቃዊ ተማሪ በመሆን ገብተው ተመረቁ።

ዞሮ ዞሮ ሞት አለና፤ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ እጅግ የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ ማክሰኞ፣ ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በተወለዱ በ፸፱ ዓመታቸው፤ በቅርብ ባደረባቸው ጽኑ ሕመም በሕክምና እየተረዱ ሳለ በካዲስኮ ሆስፒታል አርፈዋል።

፪) ሙያ፣ አስተዋጽዖ፣ ተሰጥዖ

• አዲስ አበባ በ መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ስዕሎች፣ ‘ሞዜይኮች’

• አዲስ አበባ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሚገኘው የመጀመሪያው የ’ዳግመኛ ምጽዓት ፍርድ ስዕል

• በሐረር የልዑል ራስ መኮንን ሐውልት

• በአዲግራት የ’ዳግመኛ ምጽዓት ፍርድ ስዕል

• በሎንዶን ‘ታወር ኦፍ ለንደን’ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ቤት ከብር እና ከእንጨት የተሠራ የመንበር መስቀል

• በሩሲያ፣ አሜሪካ እና በሴኔጋል ትርዒቶች የታዬው ‘የመስቀል አበባ’

• “እናት ኢትዮጵያ’

• የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ምስል

• ‘ደመራ’

• አዲስ አበባ በአፍሪቃ አዳራሽ መግቢያ የሚታየው በመቶ ሃምሳ ካሬ ሜትር ላይ የተሳለው ትላቅ የመስታወት ስዕል፤ አንዱ የአፍሪቃን የቀድሞ ዕሮሮ፤ ሁለተኛው የአኅጉሯን የወቅቱን ትግል እና በሦስተኛው ደግሞ የዚችን ትላቅ አኅጉር የወደፊት ተስፋ የሚያሳዩ ናቸው::

፫) መሰናክሎች፣ ማለፊያ ጥንካሬዎች

ፋንታሁን እንግዳ ‹ታሪካዊ መዝገበ-ሰብ› ባለው መጽሐፉ ‹‹…ትልቁ የኪነ ጥበብ ሰው ተሥፋዬ ገሠሠ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጀግና የሆኑትን አፈወርቅ ተክሌን ርዕሰ ጉዳይ አድርገው በልጅነታቸው በደረሰባቸው ‹ብልትን የመሰለብ› አደጋ ተሳልቀዋል፡፡ … ›› ብሏል፡፡ ይሄ አደጋ ከማሳለቅ ይብስ ያለ ትዳር ያለ ልጅ አስቀራቸው፡፡ በእርግጥ ወደ እድሚያቸው ማምሻ አንዲት ሴት አግብተው እንደነበርና ያልሰመረ ትዳር ሆኖባቸው ለሞታቸው አስተዋጽኦ እንዳለው ይነገራል፡፡

ሁለተኛውና የማይናቀው ፈተናቸው የማዕረጋቸው መርዘምና በሙሉ ስማቸው እንዲጠሩ መፈለጋቸው ነበር፡፡ ይህም ከብዙዎች ጋር እንዳራራቃቸው ይገመታል፡፡ ያም ቢሆን ስማቸው የልፋታቸው ዉጤት ነውና ከስሜ አንዲት እንኳ ጎድላ ብጠራ ‹አቤት አልልም› ማለታቸው ሙያቸውን ይበልጥ አስከብሮታል፡፡

፬) እጅግ የተከበሩ የዐለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌን አጥተን እንዳናጣው ነገር

ዘመናዊ ስዕልን ወደ ኢትዮጵያ ካስተዋወቁት(ገብረ ክርስቶስ ደስታ እና እስክንድርም ተጠቃሾች ነበሩ) ዋነኛው ሰው ነበሩ፡፡ በልፋት የተገኘ ረዥም ስም ያላቸው ሰው ነበሩ፡፡ ለትምህርት የላከቻቸውን ሀገራቸውን ታምነው የተመለሱ ሰው ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያን በያገሩ በጠና ያስተዋወቁ ብርቱ ሰው ነበሩ፡፡ እኛስ ያን ያህል እናውቃቸው፣ እናዘክራቸው፣ እንከተላቸዋለን ወይ?

፭) መርሆች፣ የህይወት ፍልስፍናው

ሊቁ ልበ ሙሉ ነበሩ፡፡ ኃይማኖተኛና ‹ዛሬ ከጨለመብን ይልቅ ነገ የሚበራልን ይበልጣል› ባይ ተስፈኛም ነበሩ፡፡ ዋጋ ቢያስከፍላቸውም ራሳቸውን የሚያከብሩ ክቡር ሰው ነበሩ፡፡

ምንጮቻችን

• ታሪካዊ መዝገበ ሰብ ቅጽ ሁለት፣ በፋንታሁን እንግዳ(ገጽ 187- 193)

• ኢቢኤስ የጥበብ ወሬዎች(እጅግ የተከበሩ የዐለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ)

• http://web.linkethiopia.org/guide-to-ethiopia/the-pankhurst-history-library/maitre-artist-afewerk-tekle/



አስተያየት እዚህ ያስቀምጡልን

ስም [*]ትክክለኛ ሰዉ መሆንዎን ያረጋግጡልን [*]አስተያየት እዚሁ ያስቀምጡልን


እስካሁን (0) አስተያየቶች ተሰጥተዉበታል

እጅግ የተከበሩ የዐለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

የእኔን ሥራ የሚያዩ ሁሉ ተስፋ እንዲያገኙ፣ ስለኢትዮጵያ እና ስለ አፍሪቃ ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው፣ በፀሐይ ጮራ እንዲሞቁ፣ ከሁሉም በላይ ግን “ይቻላል” የሚል እምነት እንዲኖራቸው ፍላጎቴ ነው

እጅግ የተከበሩ የዐለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ
Read in PDF 2021-09-02 በየሓ ቤተ ጥበብ


ከዚህ ቀደም ግለ ታሪካቸዉን ካቀረብንላቸዉ መካከል

ተሥፋዬ ገሠሠ ለሁሉም ጊዜ አለዉ
ተሥፋዬ ገሠሠ Read in PDF

“የወፍ ወንዱ፣ የፖለቲከኛ ሆዱ አይታወቀምና ሁሉን በብልሀት ያዙ” የሚል ምክር ከአፋቸዉ ተጨማሪ ያንብቡ



ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ ኢትዮጵያ ባንተ አልተጀመረችም ባንተም አትጠፋም፣ ትቀጥላለች!
ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ Read in PDF

ከተያያዘው ፋይል ተጨማሪ ያንብቡ



ብላቴን ጌታ ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን ያለፈ ጥረታችንን፣ ሳስታምመው ትዝ ሲለኝ ከሞከርነው ነገር ይልቅ ያልሞከርነው ነው እሚቆጨኝ፡፡
ብላቴን ጌታ ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን Read in PDF

የማይድን በሽታ ሳክም
የማያድግ ችግኝ ሳርም
የሰው ሕይወት ስከረክም
እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም።
የጋሽ ጸጋዬን ህይወት ከዚህ በላይ የሚገልጸው ቃል የለም(አራት ተጨማሪ ያንብቡ



መንግስቱ ለማ የአባቱ ልጅ፣ ቁርጠኛውና ኢትዮጵያዊውን ጸሐፌ ተውኔት፤ ለዚህ ዕትም መርጠንላችኋል፡፡
መንግስቱ ለማ Read in PDF

ምልከታው ከፊት ከአባቶቹ ዘመን፣ ከኋላ የልጆቹን ዘመን ያጠናቀረ ነበር፡፡ ዘመናዊነትን ይቀበላል፣ የአባቶቹን ባህል ግን አይተላለፍም ነበር፡፡ የህይወት አካሄዱን ልብ ብለን ያስተዋልን እነደሆነ፣ ፊት ለፊት ራሱን ለአደጋ የሚያጋፍጥ ሳይሆነ በጨዋታ እያስመሰለ የሚሸነቁጥ ዋዘኛ መሳይ ሰው ነበር፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ


መልእክተ የሓ

በዚህኛዉ ዐምድ ታሪካቸዉ እንዲቀርብ የምትፈልጓቸዉን ሰዎች እንድትጠቁሙን ወይም ደግሞ የተጻፈ ታሪካቸዉ ካለዎ በዚህ በኩል ቢያገኙን ደስታዉን አንችለዉም፡፡

መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts