ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ስነ ጽሑፍ

አጭር ልብ ወለድ


ቃል ኪዳን

Read in PDF 2023-06-12 በታደለ አያሌው

“ፍቅሪ” አለኝ፣ እንዳይነጋ የለም እድሜ ልክ ያከለብኝ ጨለማ አልፎ ረፋዱ ላይ ስልክ በመደወል።

“ሙልዬ? የኔ ጌታ! … አለህልኝ ሙሌ? አለህልኝ ወይ?” ጉልበቴ ግዉ እስከሚል ድረስ ወድቄ መሬቱን ጨምጭሜ ሳምሁት። ደስታዬ የሚያደርገኝን አሳጣኝ። ዘልዬ ሰማዩን ብስመዉ እንኳን የልቤ መድረሱን እንጃልኝ። ተመስገን! በሕይወት አለ ማለት ነዉ? በአዛኚቱ! እኔማ ስንቱን ነበር ያሰብሁት? በዚያ ላይ ስልኩ ጭምር ዝግ ሆኖብኝ በጭንቀት ልሞት ነበር። ሥራዉም በጸባዩ ብዙ ጊዜ ከብዙ አይነት ሰዎች ጋር ስለሚያዳርሰዉ፣ ክፉ ክፉዉን ብቻ እያሰብሁ እንዲችዉ ስነፈርቅ እና ስንጨዋለል ነዉ ያደርሁት። እንዲያዉ አደርሁ አልሁት እንጂ እንደዋዛ፣ አዳሬስ አዳርም አይደል።

“በደህናህ ነዉ ግን?” አልሁት፣ ወደ ነፍሴ ለመመለስ ዐይኔን ጨፍኜ እየገለጥሁ።

“ምነዉ?”

“እህእ… ምነዉ ትለኛለህ እንዴ ደሞ?”

“ምነዉ ፍቅሪ?”

“ኧረ ሙሌ በማርያም! ጭራሽ መቀለድ ሁሉ ያምርሀል? ይልቅ ንገረኝ፣ ምን ገጥሞህ ነዉ?”

“እራት ምናምን ተባብለን ነበር እንዴ ፍቅሪ?”

“ረስቸዉ ልትለኝ?”

“አይገርምሽም ረስቼዋለሁ”

“ኧረ እንዳታስቀኝ”

“አንቺን ይንሳኝ! ምን አይነት ከንቱ ነኝ በናትሽ? እንዴት ረሳሁት ግን? ለነገሩ ባልረሳዉ ነበር የሚገርመኝ እንዲያዉም። ያዉ ሥራዬን ታዉቂዉ የለ? የትናንትናዉ ደግሞ የተለየ ነበር። ብታይኝ ትንፋሼን እንኳን እንደልቤ የምተነፍስበት ፋታ አልነበረኝም። ያ ከጀርመን እያስመጣሁት ነዉ ያልኩሽ እቃ… ስለሱ አልነገርሁሽም ወይ ፍቅሪ? ነግሬሻለሁ ኧረ።… አዎ፤ እሱ እቃ ሊስተጓጎልብኝ ሲል አይገቡ ገበቼ ነዉ ለትንሽ ያተረፍሁት ብታይ። ደስ አይልም?”

“ተመስገን! እዉነት በደህናህ ነዉ?”

“ኮራሽብኝ ኣ ፍቅሪ?” አለኝ፣ ረዥሙን የእፎይታ ትንፋሼን እየደጋገምሁለት ሳለ። “ምናለ በይኝ ኋላ… ክብረት የሚሏት ነገር መድረሻ ሰማይ ካላት፣ በዚያች ሰማይ ከእኔና ከአንቺ ቀድሞ ማንም አይደርስባትም። እኔና አንቺ ብቻ! ያኔ ነዉ እኛን ማየት። መነኩሴዎች ጭምር የሚቀኑበትን ሠርግ እናሠርግና፣ ሥፍር ቁጥር በሌላቸዉ ልጆች ቤታችንን ሞልተን… ይታይሻል ኣ ኑሯችን?”

“ይሁን”

“‹ይሁን›? ምነዉ ፍቅሪ፣ አላመንሽኝም እንዴ?”

“እህእ… አሁን አለማመንን ምን አመጣዉ እዚህ? አንተን የማምነዉን ያህል የፈጠረኝንስ አምነዋለሁ እንዴ? ተዉ እንደሱ አትጠይቀኝ እንጂ ሙሌ”

የምሬን ነዉ፤ በሰማይ በምድሩ እንደሱ የምተማመንበት የለኝም። በእኔ ቤት ሀይማኖተኛ ተጨማሪ ያንብቡ


1 ከ 7

ከዚህ ቀደም ከቀረቡ አጫጭር ልብ ወለዶች መካከል
መጽሐፈ እርግማን
ታደለ አያሌዉ Read in PDF

“ግለጠዉ”

“ጭራሽ ለእኔ ነዉ ያመጣሽዉ?”

“አዎ፤ አንብበኸዋል ኣ?”

“ኧረ እኔ እንኳን ላነበዉ፣ እንዲህ የሚሉት መጽሐፍ መኖሩንም ከነጭራሹ አላዉቅም። መጽሐፈ እርግማን? ሆ! ከየት አመጣሽዉ?”

“ከዚያዉ”

“ከየት?”

“ከዚያዉ ከትናንትናዉ ስፍራ”

“ከትናንትናዉ?”

“ትናንትና እንዲህ ሆነን ተቀምጠን ተጨማሪ ያንብቡ


ቅደሚኝ
ታደለ አያሌዉ Read in PDF

“ነይ እንሂድ” ብዬ አመጣሁሽ እንጂ፣ የት እንደማደርስሽ ግን አላዉቅም። ንገሪኝ፣ በየት በኩል እንሂድ? መንገድ ነዉ ብዬ ያሳየሁሽ ሁሉ አሁን ገደል ሆኗል። የእኔ ነዉ ያልሁሽ ሁሉ ከእጄ ጠፍቷል። ከእኛ ጋር ናቸዉ ያልሁሽ ሁሉ ሄደዉ ሄደዉ አልቀዋል። ሌላዉስ ይቅር ግድ የለም። እኔ በአንቺ እድሜ ሳለሁ ተጨማሪ ያንብቡ


ቅምሻ ከገረገራ
ታደለ አያሌዉ Read in PDF

“አአአ-አየሽ ብቸኝነት መቃብር ነው። ለብቻ መቅረት ሞት አይደለም? እኔ ዓይኔ ቢታወር እመርጣለሁ። ብቸኝነት ግን ከምንም የባሰ ገሀነም ነው። የፈለገ ቢሆን ከሰው እንዳለመላመድ መጥፎ ቅጣት ያለ አይመስለኝም። ጭንቁን አይጣልብሽ! ከሰው መሀል ሆኖ በሰው እንዳለመፈለግ ያለ ጭቆና የለም። ያማል! ተጨማሪ ያንብቡ


በሁል
ታደለ አያሌው Read in PDF

ይኸው በእድሜዬ ሀገሬ የትናንቱን ያህል ከብራ ማወቋን እንጃልኝ። ዐለም ድብልቅ፣ ሠማይ እርቡቅ፣ ምድር ራቅ፣ ክብር ጥልቅልቅ ያለ ያህል ነበር አኳኋኑ መቼም። እንዲህ…

ክቡር ዶ/ር አርቲስት ማህሙድ አህመድ፣ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ፣ ሼክ ሞሓመድ አልአሙዲ፣ ጠ/ሚ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ዶ/ር ሙላቱ ተጨማሪ ያንብቡ


ግብዣ

የግል ጽሑፍዎን ወደ ቤታችን ለመላክ እዚህ ጠቅ (Click) ያድርጉ

መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts