ይኸው በእድሜዬ ሀገሬ የትናንቱን ያህል ከብራ ማወቋን እንጃልኝ። ዐለም ድብልቅ፣ ሠማይ እርቡቅ፣ ምድር ራቅ፣ ክብር ጥልቅልቅ ያለ ያህል ነበር አኳኋኑ መቼም። እንዲህ…
ክቡር ዶ/ር አርቲስት ማህሙድ አህመድ፣ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ፣ ሼክ ሞሓመድ አልአሙዲ፣ ጠ/ሚ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ ልጅ ዳንኤል ጆቴ እና ሌሎች ብዙ ሆነው በዋናው ቤተ መንግስታችን ለእራት ተቀምጠዋል። ብዙ ትላልቅ፣ ብዙ ትናንሽ ሰውም ተገኝቶ ነበር። የእራት ግብዣውን የደገሱት ጠ/ሚኒስቴሩ ናቸውና፣ የተጀመረውም በሠዐቱ ምሽት ሁለት ሠዐት ላይ ነበር። አጀማመሩ ዝምተኛ ቢሆንም ሂደቱ ማለፊያ ነበር። እንዲህ…
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ለንግግር ተነሱ ቅድሚያ። የሁሉም አይን ወደ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ። ጥሞና ሆነ በጠና። ጸጥ-ታ። ‹‹እህ›› ብለው ጀመሩ።
‹‹ጥሪ ማክበር እንደናንተ ነው። ክብረት ይስጥልኝ በቅድሚያ›› ቤተ መንግስቱ በጭብጨባ ሞላ። እሳቸው ቀጠሉ።
‹‹…ያው እንደሚታወቀው መንግስታችን መነግስትነቱ ሃያ አምስት ዐመት እየደፈነ ነው። በዚህም በኃይል ደስ ይለኛል። የሠራናቸውን ጀብዱዎች፣ ያለፍንባቸውን ፈተናዎች፣ ያፈርንባቸውን ጨዋታዎች፣ የገዛንባቸውን ዐመታቶች፣ የሆኑብንን ነገሮች ሳይ ይገርመኛል። በሁል። ኢትዮጵያችን - የተቀበልናትንና የያዝናትን፣ የነበራትንና ያደረግንላትን፣ የሆነላትንናንና የሆነልንን ሳስተያይ ቅር ብሎኛል። በሁል።››
በጠ/ሚኒስቴሩ ቅሬታ ታዳሚው ሁላ ተያየ። እሳቸው ቀጠሉ።
‹‹በተለይ መንግስታችን የሚያከብረው ማንን ነው ብዬ ዞር አልኩና ቅር ብሎኝ ዋለ በውነት። ከግንቦት እስከ ግንቦት ‹ክብር ለራሴ› የሚል መንግስት የምመራ ያህል አፈርኩ። ግንቦት ሃያን አራት ወር፣ ሕወሓትን ሁለት ወር፣ ብአዴንን ሁለት ወር፣ … እኛን ብቻ እንደምናከብር ተሰማኝ። ዕልልታችን ለእኛ ጀብዱ፣ ስብከታችን ለእኛ ርዕዮት፣ ቅጣታችን በእኛ ዕምነት … ብቻ መሠለኝና አፈርኩ። በሁል። አድዋን በዜና ያለፍን፣ የልዕልናችንን ዘመን - አክሱምን የዘነጋን፣ … ‹ወዲህ!› ያልን እየመሰለኝ ተቸገርኩ።
‹‹ከህዝብ ጋር የጋራ ታሪክ፣ ከህዝብ ጋር የጋራ ድል፣ ከህዝብ ጋር የጋራ ጀግና፣ ከህዝብ ጋር የጋራ ኑሮ ያለን አልመስልህ ብሎኝ ተዘለስኩ። በሁል። ቅር ብሎኛል እኔስ። በኃይል። በውነት። …›› ብለው ተቀመጡ። ታዳሚዎች ሁሉ በተራቸው እየተነሱ ተናዘዙ። ጥያቄው ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ቀጥሎ ከእራት በይዎች መሀል የተነሳው ማን ነበር? ተነስቶስ ምን አለ? … መልሱን አውቆ በcomment ላስቀመጠ እናደንቃለን። እስቲ እንይ። በሏ።
አስተያየት እዚህ ያስቀምጡልን
እስካሁን (3) አስተያየቶች ተሰጥተዉበታል
gashaye 2018-11-14
go ahead
Tadele Ayalew 2015-11-12
Lij Daniel Jotte, I think.
ዘመኑ አበጀ 2015-11-12
ጄኔራል (ስማቸው ማን ነበር እንኳን) ይነሱና፣ አውቀን ነው የሚል ይመስለኛል።