በህይወቴ ደርሶብኝ የማያውቅ ዝርፊያ ትናንት ተዘረፍኩ፡፡ እንዲያውም አትበድ ቢለኝ እንጂ ሁኔታው ጨርቅ የሚያስጥል ነበር፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማታ ተማሪ ነኝ፡፡ ከትምህርት መልስ እያመነታሁ ወደ ላፍቶ ሞል ብቅ ብዬ ነበር፡፡ ወደ ጌም ዞኑ ሳንዣብብ አንድ ልጅ የእጅ ምልክት ሰጠኝ፡፡ ‹ና ፑል እንጫወት› ማለቱ መሰለኝ፡፡ ሄድኩለት፡፡ ሄኖክ እንደሚባል ነገሮኝ የሚያጫውተው ሰው ይጠብቅ እንደነበር ገለጸልኝ፡፡ ፍጥነቱ አይጣል ነው መቼም፡፡ በአንድ ደቂቃ ጓደኛሞች ሆንን፡፡ እፍ አልን በቅጽበት፡፡ ጨዋታ ጀመርን፡፡ በጨዋታው መሀል እየደጋገመ እንዲህ ይለኝ ነበር፡፡ ‹‹አንተ እንዲያውም ትችላለህ፡፡ ኧረ ስንት አለ መሰለህ የኳስ ቁጥር ሁላ የማያውቅ፡፡ አሁን ትናንትና አንዱን ሶማሌ አምስት ሺ ብር ቆረጠምኩት እኮ ነው የምልህ›› ‹‹እንዴት?›› እኔ ነኝ እንዴት ባዩ፡፡ ‹‹አስይዘን ስንጫወት ነዋ፡፡ ብታይ እኮ ምንም አይችልም፡፡ ጣፍጦኛል፡፡ ዛሬ ራሱ እሱን እየጠበቅሁ ነው፡፡ ቅድም እዚያ አካባቢ እኮ ከጓደኛው ጋር አይቼው ነበር፡፡ በመጣልኝ፡፡ ዶላር እዚህ ድረስ ነው የያዘ፡፡›› ፑልን ሄኖክ ብቻ ይጫወታት! ዘንግ አያያዝ እንደሱ የሚያምርበት ሰው ይኖር ይሆን? ይራቀቅበታል፡፡ ከቆይታ በኋላ ልክ ጨዋታው ሊያልቅ ሲል ሶማሌ የተባለው ሰው መጣ፡፡ አነጋገሩ፣ ከንፈሩ፣ አኳኋኑ ሁሉ በርግጥም የሶማሌዎች አይነት ነው፡፡ እኔ ደግሞ ጥሎብኝ የምስራቅ ሰዎችን እወዳለሁ፡፡ አማርኛቸው ይጣፍጠኛል፡፡ ‹‹እ ኦርያ›› አለው ሄኖክ፡፡ ‹‹እ›› ‹‹እንጫወት?›› ‹‹መቶ አስር ነጥብ ትሰጠኛለህ?›› አለ ኦርያ እያስወደደው፡፡ ንግግሩን እኔ ስረዳው እንዲህ ሆነ እንጂ አባባሉ እንደ አባይ መንገድ ወደዚያም ወደዚህም ነው፡፡ ‹‹መቶ አስር? መቶ አስር ብዙ ነው፡፡ እንደ ትናንቱ ግን መቶ ልስጥህ?›› ‹‹አልጫወትም!›› መንገድ ጀመረ፡፡ ‹‹እሺሺ ና፡፡ ና እሺ›› እየቀፈፈኝ ብሩን እኔ ያዝኩላቸው፡፡ ኳስ ወጣላቸውና ጨዋታ ጀመሩ፡፡ ሶማሌው ፑል ገና እየለመደ ነው፡፡ አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን ዘንግ አያያዙ በራሱ ያስቃል፡፡ ኩልተፋው የአፍ ብቻ አይደለም እጁንም ይይዘዋል፡፡ ይሰነዝራል ግን ይስታታል፡፡ እንዲያው እድል ሰጥቶት ቢመታት እንኳን ኳሷ ፈቀቅ አትልለትም፡፡ አቆጣጠሩን ራሱ በቅጡ ያወቀው ስላልመሰለኝ ልመክረው ስል ያኛው ልጅ ይገላምጠኛል - ሄኖክ፡፡ በዚህ ሁኔታ አምስት መቶ ብር ተበላ፡፡ አሳዘነኝ፡፡ ‹‹እሺ አሁንስ፤ በስንት?›› ‹‹ኧረ … አንተ እኔ የብር ችግር አኮ የለብኝም፡፡ ብር በፈለከው፡፡ ግን መቶ ሃምሳ ትሰጠኛለህ?›› ‹‹መቶ ሃምሳ!? ምን ሆነህ ነው ኦርያ? … ጠረጴዛው ላይ ራሱ እኮ መቶ ሃያ እኮ ነው ያለው፡፡ መቶ ሃምሳ?›› ‹‹እንዲያውም ካንተ ጋር በቃኝ›› ኦርያ ተኮሳተረ፡፡ ድንገት ወደ እኔ ዞሮ አየ፡፡ ‹‹አንተ ግን ምንም አትችልም›› አለኝ፡፡ አንገቴን በአዎንታ ወዘወዝኩለት፡፡ የምችለውንና የማልችለውን አውቃለሁ፡፡ ፑል አይሆንልኝም፡፡ ‹‹እንዴት ቢንቅህ ነው ግን? ለምን ሰማኒያ ነጥብ ሰጥተኸው አትገጥመውም?›› አለኝ ሄኖክ፡፡ እሺም እምቢም አላልኩትም፡፡ እንዲያውም መሄድ አስቤ ነበር፡፡ እሱ ግን ሊለቀኝ አልፈለገም፡፡ ‹‹ፈርተኸው ነው?›› ይለኛል በእጅ በእግሬ እየገባ፡፡ ወደ ጠረጴዛው እየገፋፋ ዘንጉን ሰጠኝ፡፡ ተቀበልኩት፡፡ ‹‹በል አስይዝ›› አለኝ ኦርያ፡፡ ‹‹ጭራሽ በብር ነው እንዴ?እኔ አላስይዝም፡፡ ብር የለኝም፡፡›› በእርግጥም ብር አልያዝኩም፡፡ መቶ አርባ ብር ብቻ ነው በስድስቱም ኪሴ ያለው፡፡ ብይዝም ቁማር የምጫወት አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም ከቀናት በፊት ከጓደኛዬ ጋር የተሸነፈ እራት ሊጋብዝ ተወራርደን ስለበላኝ ድጋሚ እንዲያ አይነት ውርርድ ውስጥ እንደማልገባ ለራሴ ቃል ገብቼ ስለነበር ነው፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን የሰው ሃቅ የማልፈልግበት አቋም ላይ ነበርሁ፡፡ የኔ የሆነውን አሳልፌ አልሰጥም፣ የኔ ያልሆነውን አልመኝም የሚል ፍልስፍና የጀመርኩበት ወቅትም ስለሆነ ቁማሩን አልወደድሁትም፡፡ ግን ሄኖክ በዋዛ ሊላቀቀኝ አልፈለገም፡፡ ‹‹ለምን ሰማኒያ ነጥብ በአምስት መቶ ብር አትጫወቱም?›› ‹‹የለኝማ፡፡›› ‹‹ግድየለም ቆይ …›› ብሎ ግራ ቀኝ መቃበዝ ጀመረ፡፡ ኦርያና እኔ ዝም ደግሞ ብለን የሚሆነውን ጠበቅን፡፡ ወደ ባንኮኒው አካባቢ ወዲያ ወዲህ የሚል አንድ ልጅ ወደ እኛ መጣ፡፡ ‹‹በእናትሽ ነፍሴ ለዚህ ልጅ የሆነ ያህል ብር አታበድሪውም?›› አለው፡፡ ‹‹ስንት ፈልገሽ ነው?›› አለኝ የታሰረ ብር አውጥቶ፡፡ ቆዳው ጅል መሰለኝ፡፡ ‹‹አይይ…›› ስል ‹‹አምስት መቶ ብር ስጭው›› አለ ሄኖክ ቀልጠፍ ብሎ፡፡ ያኔ ይሉኝታ ይሁን ምን እንጃ ብቻ ሄኖክን መቃወም ከበደኝ፡፡ ተቀበልኩት፡፡ ‹‹ግን የሂሳብ ብር ነው፡፡ ኤቲኤም ይዘሻል አይደል?›› ‹‹አዎ፡፡ የዳሽንም የንግድ ባንክም አለኝ፡፡›› ብዬ ቦርሳዬን ከፍቼ አሳየሁት፡፡ ‹‹እስኪ ለማንኛውም ሞባይልሽን ልያዘው›› ብሎ ተቀበለኝ፡፡ ኦርያም ያን ያህል ብር አውጥቶ አስያዘ፡፡ የብር መዐት ይዟል፡፡ ስንት ይሆን? ጨዋታ ጀመርን፡፡ እንደቅድሙ ሁሉ መውሸልሸል ጀመረ፡፡ በዚህ ሰዐት እኔ እኔ አልነበርኩም፡፡ አዛዡ ሄኖክ ነው፡፡ ኦርያ ዞር ሲል ኳሷን ያስተካክልልኛል፡፡ ልክ ላሸንፈው ስቃረብ ሄኖክ አንድ ሃሳብ አመጣ፡፡ ‹‹ለምን በኳስ አትጫወቱም?›› ‹‹እንዴት›› አለ ኦርያ፡፡ ‹‹ለምሳሌ አሁን የምትጫወቱት ዐሥርን አይደል? … ለምን እሷን በማስገባት አትጫወቱም፡፡ ዋናው እንዳለ ሆኖ ለምሳሌ አምስት መቶ ብር ብታስይዙ እሷን ያስገባ ይበላል ማለት ነው፡፡›› ‹‹እሺ›› አለ ኦርያ ቀድሞ፡፡ እኔ ግን ብር የለኝም፡፡ አበዳሪው በችኮላ ተጠራ፡፡ ጠሪው እኔ አይደለሁም ሄኖክ ነው፡፡ ‹‹አትጨምሪለትም በናትሽ?›› ሄኒዬ ተቅለሰለሰበት፡፡ ‹‹ስንት?›› ‹‹አምስት መቶ፡፡›› ‹‹ኧረ ይሄ ነገር … ትሰጭኛለሽ አይደል ግን?›› እያመነታ ሰጠኝ፡፡ ከኦርያ ጋር ሌላ አምስት መቶ ብር አስያዝን፡፡ እሱ ቀድሞ ሞከረ ሳታት፡፡ እኔ ግን አስገባኋት፡፡ በላሁት ማለት ነው፡፡ ‹‹ዐስራ አንድን ቀድሞ ያስገባ … በአንድ ሺ?›› አለኝ ኦርያ፡፡ አሸነፈኝ፡፡ ከዚያስ? ከዚያማ የሆነውን እንጃ፡፡ ብቻ ግን አስራ ሥስት ሺ ብርና ሞባይሌን እንደተበላሁ አሁን ወደ ቀልቤ ስመለስ አረጋገጥሁ፡፡ ይኸን ለማጠረቃም ያልኩትን ደፋ ቀና ግን እኔና እግዜሬ እናውቀዋለን፡፡ ፈትነው ጣሉኝ፡፡ ወደቅሁላቸውና ፈጠፈጡኝ፡፡ ጥሬ ፍልስፍናዬ ላይ ነው እንትፍ ያሉበት፡፡ ደሜን ግን ይልቁን ያንተከተከው የገዛ ወዳጄ ነው፡፡ ለካንስ በእሱም ደርሶበት ኖሮ ኦርያንም፣ ሄኖክንም አበዳሪውንም ያውቃቸዋል፡፡ ስራቸው ነው፡፡ ‹‹ለምን አልነገርከኝም ነበር ታዲያ?!›› ልሰለቅጠው ምንም አልቀረኝ፡፡ ‹‹አፍሬ ነው ባክሽ፡፡ መዘተሬን ብነግርህ አፍህን አልችለውም ብዬ ነዋ፡፡›› በሉ ጅቦችን ሳይሄዱ ለወዳጆቻችሁ ንገሯቸው፡፡ ጅቦቹ ላይ ውሻ እንልቀቅባቸው፡፡ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስም [*]ትክክለኛ ሰዉ መሆንዎን ያረጋግጡልን [*]አስተያየት እዚሁ ያስቀምጡልን
እስካሁን (1) አስተያየቶች ተሰጥተዉበታል
Biniam B. 2017-11-27I get it.
በህይወቴ ደርሶብኝ የማያውቅ ዝርፊያ ትናንት ተዘረፍኩ፡፡ እንዲያውም አትበድ ቢለኝ እንጂ ሁኔታው ጨርቅ የሚያስጥል ነበር፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማታ ተማሪ ነኝ፡፡ ከትምህርት መልስ እያመነታሁ ወደ ላፍቶ ሞል ብቅ ብዬ ነበር፡፡ ወደ ጌም ዞኑ ሳንዣብብ አንድ ልጅ የእጅ ምልክት ሰጠኝ፡፡ ‹ና ፑል እንጫወት› ማለቱ መሰለኝ፡፡ ሄድኩለት፡፡ ሄኖክ እንደሚባል ነገሮኝ የሚያጫውተው ሰው ይጠብቅ እንደነበር ተጨማሪ ያንብቡ
እኔ የምሰራበት መስሪያ ቤት ሶስት እና አራት መቶ ሰራተኞችን የሚያተራምስ፣ በብዙ ሚሊዮኖች ብር እየቆጠረ የሚያገለባብጥ ከስም ሁሉ ተመርጦ ታላቅ ስም የተሰጠው ነው፡፡ አንዳች የሚሰራው ስራ የለውም እንጅ፡፡ ስሙን ግን ተሸክሞታል፡፡ለነገሩ ስሙ መስሪያ ቤቱን ተሸክሞታል ቢባል ይሻላል፡፡ ምክንያቱም የመስሪያ ቤቱ ህልውና ያለው በስሙ አማካኝነት እንጅ በስራው አይደለምና፡፡በስራው ቢሆን ኖሮማ እኔ ወደዚያ መስሪያ ቤት ሳልገባ ተጨማሪ ያንብቡ
የግል ጽሑፍዎን ወደ ቤታችን ለመላክ እዚህ ይጫኑ
ለገሀር፣ አዲስ አበባ
19686
yehaarts@gmail.com
+251 912 944937
“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።
(2015-2024) © yehaarts