አንድ ያልዘፈነ ዘፋኝ እንደሚከተለው አምቧቀሰ፡፡ ‹‹ልጅ ሆነን ከወንድሞቼ ጋር ለጉድ እንበሻሸቅ ነበር፡፡ እናታችን ምሳችንን ታኖርልንና ወደ ሰንበቴ ትሄዳለች፡፡ ከዚያ እኛ እጃችንን ልንታጠብ ተማምለን እንወጣለን፡፡ ከመካከላችን አንዱ አዘናግቶን ይንደረደርና ወደ ቤት ገብቶ ቤቱን በውስጥ ይዘጋዋል፡፡ ብቻውን ሊበላ፡፡ እኛም እያባበልነው በሩን እንቆፈቁፋለን፡፡ እናባብለዋለን፡፡ እንለምነዋለን፡፡ እናስፈራራዋለን፡፡ ‹‹ኧረ ተው ግን ተው?›› እንለዋለን፡፡ የባሰበት እንደምንም ጥርሱን ነክሶ፣ ጅማቱ እስኪወጣ ገፍቶ ይገባል፡፡ ከዚያ እሱም ከኛ ወገን እንዳልነበር ይሆናል፡፡ ተጋግዘው በሩን በውስጥ ያጠብቃሉ፡፡ እንደገና ሁለቱን እናባብላለን፡፡ እንደገና እንለማመጣለን፡፡ እነሱን እንታገላለን፡፡ ላይከፍቱልን ነገር፡፡ ውጭ ሳለን አብሮ እንዳልራበን ወስጥ ሲገቡ ይክዱናል፡፡ … ያኔ ያለው ረሃብ! ብስጭቱ! እልሁ! … እናም ብሶቱ የጋለበትና ጉልበቱ የጠናለት እንደምንም ፏጭሮ ይገባና እኛን ክዶ ከቀደሙት እንዳንዱ ይሆናል፡፡ ቀሪዎቻችን እንዲሁ ጦም እንውላለን፡፡›› ይኸው ዘፍኖ የማያውቀው ዘፋኝ ከዚያ እስካሁን በሩ ላይ ቆሟል፡፡ ያንኳኳል የሚከፍትለት፣ ይገፋል የሚሸነፍለት፣ ያባብላል የሚራራለት፣ ይጮሃል የሚሰማው የለም፡፡ የቀደሙት ዘግተውትበት በሩ ላይ ነው ይኸው፡፡ እና ጉበኑን አንቆ ታንቆ ሊሞት! ምኞቱ ዘፋኝ መሆን፣ ኑሮው የቀደሙትን መማጠን፡፡ ጉበኑን ቢከፍቱለት፣ ከነሱ ይልቅ ሊዘፍን ይመኛል፡፡ እና ቀድመው አንድም ተፍጨርጭረው አንድም እንደዋዛ የገቡት በሩን በውስጥ አጥብቀው ዘግተውበታል፡፡ ወይ ዘፍነው የልብ አያደርሱ፣ ወይ በሩን ከፍተው ተቀባይ አያስገቡ እንዲያው ሲያሳዝን! ወይ እዚሁ ሲጠብቅ መሞቱ ነው፤ ወይ እንሱ እንደገቡት ለመግባት ጅማቱ መውጣቱ ነው፡፡ ምስኪን የኔብጤ? ለነገሩ እሱ ብቻ አይደለም መግቢያ ያጣ፡፡ ገዢው እንትን የቋመጡ እንትኖችን እንዲህ ዘግቶባቸዋል፡፡ በመከራ ተማርን እሚሉ መምህራን ተማሪዎች ላይ እንዲህ ዘግተዋል፡፡ በመከራ የታወቁ ደራስያን በጀማሪዎቹ ላይ እንዲህ ዘግተውባቸዋል፡፡ በመከራ የከበሩ ነጋዴዎች በጥቃቅኖቹ ላይ እንዲህ ዘግተውባቸዋል፡፡ … በርግጥ አገባቡ ለየቅል ነው፡፡ አንዱ አፈር ልሶ፣ አንዱ እንደዋዛ ይገባል፣ ሌላውም እንዲያ ይገባል፡፡ ገብተው ግን ከቀደሙት እንዳንዱ መሆን እንጂ ዞረው አያዩም፡፡ ‹‹በዚህ ነው ጉበኑ›› አይሉም፡፡ ‹‹ከፈለጋችሁ እኛ አጎንብሰን እንደገባን አጎንብሳችሁ ግቡ›› እንጂ ሌላ መግቢያ አይከፍቱም፡፡ እንዲያውም የእነሱ ዐላማ እኛ እንድንገባ ሳይሆን እንዴት ሲገቡ እንዴት ፍዳቸውን እንደበሉ እንድናውቅላቸው ብቻ ነው፡፡ ኧረ ተው ግን ተው!
ስም [*]ትክክለኛ ሰዉ መሆንዎን ያረጋግጡልን [*]አስተያየት እዚሁ ያስቀምጡልን
እስካሁን (1) አስተያየቶች ተሰጥተዉበታል
ስም ያልጠቀሰ 2015-06-26ምኑን ጠቀስሽው ላሌ? የተዘጋበት እኮ ያልዘፈነው ዘፋኝ ብቻ አይደለም፡፡ ጀማሪው ነጋድራስ ብቻ አይደለም፡፡ ሹመኛው ብቻም አይደለም፡፡ መምህሩ ብቻም አይደል በተማሪው የዘጋበት፡፡ … ሾፌሩ ቀድሞ መሙን ከያዘ ዘግቶ ቀጥ! ስራ አጥ ስራ ሲይዝ ባልያዙት ላይ ጉበኑን አጥብቆ ቁጭ! ሴት ከወንድ እኩል ስትሆን ያልሆኑትን ረስታ ጸጥ! … አሸን ነው ብንዘረዝረውስ፡፡ ግን እንተወዋለን፡፡
በህይወቴ ደርሶብኝ የማያውቅ ዝርፊያ ትናንት ተዘረፍኩ፡፡ እንዲያውም አትበድ ቢለኝ እንጂ ሁኔታው ጨርቅ የሚያስጥል ነበር፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማታ ተማሪ ነኝ፡፡ ከትምህርት መልስ እያመነታሁ ወደ ላፍቶ ሞል ብቅ ብዬ ነበር፡፡ ወደ ጌም ዞኑ ሳንዣብብ አንድ ልጅ የእጅ ምልክት ሰጠኝ፡፡ ‹ና ፑል እንጫወት› ማለቱ መሰለኝ፡፡ ሄድኩለት፡፡ ሄኖክ እንደሚባል ነገሮኝ የሚያጫውተው ሰው ይጠብቅ እንደነበር ተጨማሪ ያንብቡ
እኔ የምሰራበት መስሪያ ቤት ሶስት እና አራት መቶ ሰራተኞችን የሚያተራምስ፣ በብዙ ሚሊዮኖች ብር እየቆጠረ የሚያገለባብጥ ከስም ሁሉ ተመርጦ ታላቅ ስም የተሰጠው ነው፡፡ አንዳች የሚሰራው ስራ የለውም እንጅ፡፡ ስሙን ግን ተሸክሞታል፡፡ለነገሩ ስሙ መስሪያ ቤቱን ተሸክሞታል ቢባል ይሻላል፡፡ ምክንያቱም የመስሪያ ቤቱ ህልውና ያለው በስሙ አማካኝነት እንጅ በስራው አይደለምና፡፡በስራው ቢሆን ኖሮማ እኔ ወደዚያ መስሪያ ቤት ሳልገባ ተጨማሪ ያንብቡ
የግል ጽሑፍዎን ወደ ቤታችን ለመላክ እዚህ ይጫኑ
ለገሀር፣ አዲስ አበባ
19686
yehaarts@gmail.com
+251 912 944937
“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።
(2015-2024) © yehaarts