ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ዐውደ ዜና

ሰሞነኛ ወሬዎች፣ አዳዲስ ነገሮች፣ የመርሐ ግብር ጥቆማዎች

ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ የጠሩት ይፋዊ ትብብር ሳይሰምር ቀረ፡፡

ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ የጠሩት ይፋዊ ትብብር ሳይሰምር ቀረ፡፡

 ታደለ አያሌዉ       2015-07-10

‹ጤዛ›፣ ‹ቡሽ ማማ›፣ ‹አድዋ›፣ ‹ሳንኮፋ›ንና ሌሎች አበይት ፊልሞችን የሠሩት ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በሰኔ ወር መግቢያ ነበር ጥሪያቸውን በይፋ ያስተላለፉት፡፡ የጋራ ታሪክ በጋራ እንስራ ሲባልም የ‹ጡት ልጅ› ጥሪ የመጀሪያው ነበር፡፡ ‹‹በ60ዎቹ መግቢያ ላይ ስለነበረችዋ የ13 ዐመት ጨቅላ(አይናለም) የሚተርከውን ይህን ፊልም አብረን እንስራው›› ብለው፡፡ ‹‹ታሪኩ የኛው ነውና እኛው ሰርተን እኛው እንየው›› ብለው፡፡ ፊልሙን በቀላል ወጭ ሰርቶ ለመጨረስ ከሚያስፈልገው ግማሽ ሚሊዮን ዶላር ከህዝብ የሚገኝበትን መንገድ ሲጠቁሙ አስተባባሪዎች በይፋ እንደገለጹት በፌስቡክ፣ በቲዊተር፣ በሃሽታግ፣ በኢንስታግራምና ሌሎች መንገዶች ቅስቀሳው በትብብር እንዲሄድ ነበር፡፡ ነገር ግን በእቅዱ መሰረት በሀምሌ መግቢያ ብሩ ተሟልቶ ወደ ቀረጻ ይገባል ቢባልም የጥሪው አጸፋ እምብዛም ሳይሰምር ቀረ፡፡

‹‹በእርግጥ በበኩሌ በጥሪያቸው መሰረት የምችለውን አድርጊያለሁ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ በፌስቡክና በቲዊተር ገጾቼ ጥሪዉን ለወዳጆቼ ሳጋራ ነበር፡፡ ምክንያቱም ኃይሌ ገሪማን ያህል ፕሮፌሰር አፍ አውጥቶ እንተባበር ሲል ዝም ብል ኖሮ ኋለኝነት ነበር፡፡ ያም ሆኖ ግን በየሽልማት መድረኩ እያኮራን የነበረን ታላቅ ሰው ቆሞ አግዙኝ ሲል ባገዝኩት ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ግን አቅሙን ከየት ላምጣው፡፡ ስለዚህም አቅሙ ያላቸው ከጎኑ እንዲቆሙ ነው የኔም ጥሪ፡፡›› ቤታችን የሀ ቤተ ጥበብ ያናገው አንድ የፕሮፌሰሩ አድናቂ ነው እንዲህ ያለ፡፡ በእርግጥም የእኛን ታሪክ በእኛው ቋንቋ በእኛው አቅም እንስራው ማለቱ ቅዱስ ሀሳብ ነውና ‹‹መኩሪያችንን እናኩራው›› የብዙ አስተያየት ሰጭዎች ጥሪ ነው፡፡ የእኛም ጭምር፡፡

32 ከ 33

ሊያጋሩን የሚፈልጉት መረጃ (የዜና ጥቆማ) ካለዎ ያግኙን

መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts