ገ ረ ገ ራ     በማንኛዉም የመጽሐፍ አዟሪና መደብር ይገኛል።     Order4Delivery (እዚሁ ያዝዙ)
ዐውደ ዜና

ሰሞነኛ ወሬዎች፣ አዳዲስ ነገሮች፣ የመርሐ ግብር ጥቆማዎች

የ18ኛው ‹አዲስ ዓለም አቀፍ የፊልም ድግስ› (AIFF) መክፈቻዉ ደረሰ

የ18ኛው ‹አዲስ ዓለም አቀፍ የፊልም ድግስ› (AIFF) መክፈቻዉ ደረሰ

 ታደለ አያሌዉ       2024-05-11

በተለይም የአፍሪካ ስመ ጥሩ የፊልም ሰሪዎች ከሀገር ዉስጥ የፊልም ቤተሰቦች ጋር ገጽ ለገጽ የሚያገናኘዉ ዓለም አቀፍ የፊልም ድግስ በሚመጣዉ ረቡዕ (ግንቦት 7፣ 2016ዓ.ም) አመሸሽ ላይ እንደሚከፈት ከአዘጋጆቹ የደረሰን ኢ-ሜይል ይገልጣል፡፡ ረቡዕ ዕለት ጥሪ የተደረገላቸዉ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ሌሎች ታላላቅ እንግዶች ሁሉ በተጋበዙበት በጣልያን ባህል ማዕከል መክፈቻዉን ያደርግና፣ እስከ ሳምንቱ ማብቂያ እሁድ (ግንቦት 11፣ 2016ዓ.ም) ድረስ የኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የተመረጡ ዘጋቢ ፊልሞች በጀርመን ባህል ማዕከል (GOETHE)፣ በፈረንሳይ ባህል ማዕከል (Alliance Éthio-Française) እና በጣልያን ባህል ማዕከል ሲታዩ እና ዉይይት ሲደረግባቸዉ ይሰነብታሉ፡፡

መግቢያ፡ በነጻ

ዝርዝር መርኃ ግብሩን ለማወቅ፡ ምስሉን ይመልከቱ

ተጨማሪ መረጃዎች፡

www.addisfilmfestival.org

+251933714860

+251116622640/41

2 ከ 33

ሊያጋሩን የሚፈልጉት መረጃ (የዜና ጥቆማ) ካለዎ ያግኙን

መገኛችን

ለገሀር፣ አዲስ አበባ

19686

yehaarts@gmail.com

+251 912 944937

ጉርሻ - Bonus

“ከፊደል ሀ፣ ከከተማ የሓ የሚቀድም የለም” ተብሏል፡፡ የአጋዝያን ምድር፣ የግዕዝ ቋንቋም መነሻ፣ የልዕልናችንም መጀመሪያ ነበረች፡፡ በብዙ ጥበብ የተንበሽበሽች፡፡ አሁን እምብዛም ሞቋት የማታድረዋ የሓ፤ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሁነኛ ዋና ከተማ ነበረች።

(2015-2024) © yehaarts